አገልግሎቱ ለባቡል ኸይር በጎ አድራጎት ድርጅት የኢፍጣር መርሀ-ግብር አካሄደ
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨
የኢትዮጵያ መድኃኒት አቅራቢ አገልግሎት ትላንት ማምሻዉን ባቡል ኸይር ድርጅት ዉስጥ ለሚገኙ ሙስሊም ማህበረሰቦች እና ለተቸገሩ ወገኖች የኢፍጣር መርሀ ግብር ያካሄደ ሲሆን ፤ በመርሀ-ግብሩ የአገልግሎቱ ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር አብዱልቃድር ገልገሎ ፤ም/ዋና ዳይሬክተር አቶ ሰለሞን ንጉሴ ፤ ዳይሬክተሮች እና ሰራተኞች እንዲሁም የባቡል ኸይር በጎ አድራጎት ድርጅት መስራች ወ/ሮ ሀናን ሙሀመድ ታድመዋል፡፡
የመርሀ-ግብሩ ዋና አላማ ከማህበረሰባችን ጋር መቀራረብን በመፍጠር ሁላችንም ከፈጣሪ ዘንድ ምስጋና ለማግኘት ነዉ ሲሉ የአገልግሎቱ ዋና ዳይሬክተር ተናግረዉ ፤ የተቸገሩ እና የተራቡ ወገኖችን ማብላት ከፈጣሪ ዘንድ ትልቅ ቦታ አለዉ እና ወ/ሮ ሀናን ለምታደርገዉ በጎ ስራ ምስጋናየ ከፍ ያለነዉ ብለዋል ፡፡
አገልግሎቱ ከዚህ በፊትም የህክምና ግብአቶችን ከማቅረብ ጎን ለጎን ማህበራዊ ኃላፊነቱን በመወጣት በመድኃኒት ፣ በአልባሳት ፣ በገንዘብ እና በተለያዩ ነገሮች ድጋፍ ሲያደርግ መቆየቱን የአገልግሎቱ ሴቶች ፣ ህፃናት እና ወጣቶች ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ወ/ሮ አለምፀሀይ ዳታ ተናግረዉ ፤ በቀጣይም እንደነዚህ አይነት እና መሰል ተግባራትን አጠናክረዉ እንደሚቀጥሉ ገልፀዋል፡፡
ረመዳን የእዝነት ወር በመሆኑ በዚህ ቀን ተሰባስባችሁ ፈጣሪ የሚወደዉን መርሀ -ግብር በማዘጋጀት ላደረጋችሁልን የኢፍጣር መርሀ- ግብር ምስጋናየ ላቅ ያለ ነዉ ሲሉ የበጎ አድራጎቱ መስራች ወ/ሮ ሀናን ተናግረዋል ፡፡
#ማገልገል ክብር ነዉ
ሰላም ይደግ