ኤጀንሲው ለስኳር ህክምና አገልግሎት የሚውሉ መድኃኒቶችን አሰራጨ፡፡……………………………….
December 30, 2020Uncategorized @am
የኢትዮጲያ መድኃኒት አቅራቢ ኤጀንሲ ለስኳር ህሙማን ህክምና አገልግሎት የሚውሉ Insulin Soluble Human ፣ Insuline Isophane Biphasic እና Insulin Isophane Human (suspension) የተባሉ መድኃኒቶችን ከህዳር 28 ቀን 2013 ዓ.ም ጀምሮ ማሰራጨቱን የመጋዘን አያያዝና ክምችት አስተዳደር ወ/ሪ ስምረት የማነ አስታወቁ፡፡Insulin Soluble Human ፣ Insuline Isophane Biphasic እና Insulin Isophane Human (suspension) ለስኳር (Diabetes mellitus ) አይነት 1ና2 (Type 1 and Type 2) ህሙማን የሚውሉ መድኃኒቶች መሆናቸውን ባለሞያዋ ገልጸዋል፡፡ስርጭቱም በኤጀንሰው 18 ቅርጫፎች አማካኝነት ለጤና ተቋማት ተደራሽ በማድረግ ላይ የሚገኝ ሲሆን 25 ሚሊዮን 967 ሺህ 897 ብር ወጪ እንደተደረገባቸው ወ/ሪ ስምረት ተናግረዋል፡፡
ሂሩት ኃይሉ