ኤጀንሲው ለስኳር በሽታ የሚውሉ መድኃኒቶች ማስገባቱን ገለፀ፡፡
November 22, 2019ፊውቸርድ ዜና
ኤጀንሲው ለስኳር በሽታ የሚውሉ Insulin Isophane Human100.Iu/ml in 10 ml injection ማስገባቱን የመደበኛ መድኃኒት ግዥ ባለሞያ ወ/ሮ ሜቲ ገመቹ ዛሬ ህዳር 11 ቀን 2012 ዓ.ም. አስታወቁ፡፡
ወ/ሮ ሜቲ መድኃኒቶቹ (61) ፓሌት እንደሆኑና በህዳር ወር መግቢያ ላይ በዋናው መ/ቤት Main 3 እና አዲስ አበባ ቁጥር 2 ቅርንጫፍ መጋዘን መግባታቸውን ባለሞያዋ ገልጸዋል፡፡
መድኃኒቶቹ ከ325 ሺህ የአሜሪካ ዶላር በላይ ወጪ እንዳላቸው አስታውቀው ጤና ተቋማት መጥተው መውሠድ እንደሚችሉ ባለሙያዋ ተናግረዋል፡፡
ይህ መድኃኒት በደም ውስጥ ያለውን የስኳር መጠን ለመቆጣጠር እንደሚረዳ ባለሙያዋ አክለዋል፡፡
በጸሎት የማነ