ኤጀንሲው ከ14 ሚሊዮን በላይ ሰዎች ማከም የሚያስችል የትራኮማ መድኃኒት በማሰራጨት ላይ ነው ===================
March 9, 2020ፊውቸርድ ዜና
የኢትዮጵያ መድኃኒት አቅራቢ ኤጀንሲ ከ14 ሚሊዮን በላይ ሰዎች ማከም የሚያስችል 971 ሚሊዮን 442 ሺ 127 ብር ወጪ ያላቸው ለሁለተኛው ዙር ዘመቻ (የማህበረሰብ መር ጅምላ የመድኃኒት እደላ) አገልግሎት የሚውሉ የትራኮማ መድኃኒቶች ማሰራጨት መጀመሩን የአቅርቦት ሠንሠለት አማካሪ የሆኑት አቶ ዳንኤል ተፈሪ የካቲት 11 ቀን 2012 ዓ.ም ገለፁ፡፡
ኤጀንሲው እያሰራጨ ያለው የትራኮማ መድኃኒቶች ማለትም Azithromycin Suspension, Azitromycin Tablet እና Tetracycline 1% eye ointment በአማራ፣ በኦሮሚያ፣ በትግራይ እና በደቡብ ክልሎች ለሚገኙ 82 ወረዳዎች ሲሆን ዘመቻው በጤና ተቋማት ከሚያዝያ ወር ጀምሮ የሚሰጥ ነው ብለዋል፡፡
በተመሳሳይ ዜና ኤጀንሲው የመጀመሪያ ዙር ዘመቻ (የማህበረሰብ መር ጅምላ የመድኃኒት እደላ) በጥቅምት ወር ያሰራጨ ሲሆን ከ 24.6 ሚሊዮን በላይ ሰዎችን ሊያክም የሚችል 1.7 ቢሊዮን ብር በላይ ዋጋ ያላቸው የትራኮማ መድኃኒቶች ከላይ ከተገለጹት አራት ክልሎች በተጨማሪ በአፋር፣ በቤንሻንጉል፣ በጋምቤላ እና በሶማሌ ክልሎች ለሚገኙ ወረዳዎች ስርጭት ተካሂዷል፡፡
በአጠቃላይ በሁለቱም ዙር የትራኮማ መድኃኒቶቹ 36.3 ሚሊዮን በላይ የሆኑ ሰዎችን ማከም የሚችል 2.7 ቢሊዮን ብር የሚጠጋ ዋጋ ያላቸው ናቸው፡፡