ኤጀንሲው የቲቢና የስጋ ደዌ በሽታዎችን ለማከም የሚውሉ መድኃኒቶች አሰራጩ
የኢትዮጲያ መድኃኒት አቅራቢ ኤጀንሲ ከ 428 ሚሊዮን ብር በላይ ዋጋ ያላቸው የቲቢና የስጋ ደዌ በሽታዎችን ለማከም የሚውሉ መድኃኒቶችና ግብዓቶች ማሰራጨቱን የቲቢና የወባ ተወካይ የሆኑት ወ/ት ሜሮን ያቆብ ነሐሴ 21 ቀን 2012 ዓ.ም ገለጹ፡፡
ኤጀንሲው TB kit ፣ RHZ እና RH መድኃኒቶቸን ያሰራጨ ሲሆን 428 ሚሊዮን 826ሺህ 613 ብር ወጪ እንዳላቸው ባለሞያዋ አብራረተዋል፡፡
ግብዓቶቹም በኤጀንሲው ቅርጫፎች አማካኝነት በሁሉም ክልሎች በ2012 በጀት ዓመት የተሰራጩ ሲሆን 150ሺህ 400 ሰዎች ማከም እንደሚያሰችል ተገልጾዋል፡፡
ሂሩት ሀይሉ