ኤጀንሲው Cross dock እያከናወነ መሆኑ ተጠቆመ፡፡ ———————————–
March 20, 2020ፊውቸርድ ዜና
የኢትዮጵያ መድኃኒት አቅራቢ ኤጀንሲ ለፈጣን አገልግሎት /Cross dock/ ትልልቅ ጭነት ያላቸው መድኃኒቶችንና የሕክምና መገልገያ ግብዓቶችን በቀጥታ እያሠራጨ መሆኑን የመጋዘን አያያዝና ክምችት ባለሙያ ወ/ት ኑሃሚን ኤልያስ ዛሬ መጋቢት 11 ቀን 2012 ዓ.ም. አስታወቁ፡፡
እንደ ባለሙያዋ ገለፃ ኤጀንሲው ግብዓቶቹ ወደ መጋዘን ሣይራገፉ ከኮንቴነሩ በቀጥታ ለኤጀንሲው 19 ቅርንጫፎች ስርጭት እንደሚካሄድና በአሁኑ ሠዓትም የሕክምና መገልገያ ግብዓቶችና ለስነ ተዋልዶ አገልግሎት የሚውሉ መድኃኒቶች እየተሠራጩ እንደሚገኙ አብራርተዋል፡፡
ይህ ተሞክሮ ካለፈው አመት እየተካሄደ መሆኑንና በአሁኑ ወቅት ግን ያለውን የመድኃኒት ማከማቻ መጋዘን ጥበት ከመቀነስ አንፃር ስርጭቱን የበለጠ በማጠናከር እየተሠራ መሆኑን ወ/ት ኑሃሚን በቃለ ምልልሱ ተናግረዋል፡፡
ስርጭቱ እጅ በእጅ ዝውውር እየተካሄደ እንደሆነ እንዲሁም ለሞጆ ደረቅ ወደብ /ለኮንቴነር/ የሚከፈል ክፍያ ወጪን እንደሚቀንስና ጊዜን በመቆጠብ ለጤና ተቋማት በፍጥነት ተደራሽ ለማድረግ Cross dock ጠቀሜታው የጎላ መሆኑ ተገልጿል፡፡