የህንድፋርማሲዩቲካልኤክስፖርትፕሮሞሽንካውንስል (PHARMEXCIL) የሚመራዉየፋርማስዩቲካልድርጅቶችንየያዘየልዑካንቡድንከአገልግሎቱከፍተኛአመራሮችጋርተወያዩ
የህንድ የፋርማሲዩቲካል ኤክስፖርት ፕሮሞሽን ካውንስል (PHARMEXCIL) የሚመራዉ የፋርማሲዩቲካል ድርጅቶችን የያዘ የልዑካን ቡድን ከአገልግሎቱ የጤና ስርአት ማጠናከሪያና ፋይናንስ ዘርፍ ም/ዋና ዳይሬክተር አቶ አቅናው ካውዛ እንዲሁም ከግዥ አስተዳደር ዘርፍ ም/ዋና ዳይሬክተር አቶ ሰለሞን ንጉሴ ጋር ህዳር 11/2016 ዓ.ም ተወያይተዋል።
በውይይቱ ሰለ አገልግሎቱ ስትራቴጂክ እቅዶች፣ ሰለ አቅርቦት ሰንሰለት ስርአት፣ በፋርማሲዩቲካልና በጤናው ዘርፍ በሁለቱ ሀገራት መካከከል ያለውን ኢንቨስትመንት ይበልጥ በማጠናከር ባለሀብቶቹ በሀገር ውስጥ ያለውን መልካም እድል ተጠቅመው መዋለ ነዋያቸውን በማፍሰስ በሀገር ውስጥ ምርት ኢንቨስት እንዲያደርጉ አቶ ሰለሞን ንጉሴ ለልዑካን ቡድኑ ያቀረቡ ሲሆን፤ በተለይም የአገልግሎቱ የጨረታ ስርአት ምን እንደሚመስል ፣ የግዥ ስርአት እና የግብአቶች የወደብ ላይ ቆይታ ሁኔታ ዙሪያ በሰፊው ዉይይት አድርገዋል።
በቂ አቅራቢ የሌላቸውን የህክምና ግብአቶች የተለዩ በመሆኑ ምርቶቹን በሀገር ውስጥ በማስመዝገብ የህንድ ፋርማሲዩቲካል ኩባንያዎች ከዘርፍ ተጠቃሚ ሊሆኑ ይገባል የተባለ ሲሆን ከህንድ ፋርማስዩቲካል ኤክስፖርት ፕሮሞሽን ካውንስል ዋና ዳይሬክተር ራቪ ኦዳያ አንደተናገሩት የኢትዮጵያ መድኃኒት አቅራቢ አገልግሎት የህክምና ግብአቶችን ከህንድ ሀገር በማስመጣት ሰፊ ትስስር ያለው ተቋም በመሆኑ ቀጣይም አጠናክረው አንደሚቀጥሉ ጠቁመዋል።
#ማገልገል ክብር ነው
ሰላም ይደግ