የምዕራብ ክላስተር የ3.9 ቢሊየን ብር መድኃኒቶች ማሠራጨቱን ገለፀ፡፡
September 18, 2019ፊውቸርድ ዜና
የምዕራብ ክላስተር 3.9 ቢሊየን ብር በላይ መድኃኒቶችና የሕክምና መገልገያ መሣሪያዎች ስርጭት ማካሄዱን በ3ተኛው የአቅርቦት ሠንሠለት መድረክ የጅማ ቅርንጫፍ ሥራ አስኪያጅ አቶ መለስ ተክሌ አስታወቁ፡፡
የምእራብ ክላስተር ጅማ፣ ነቀምት፣ ጋምቤላ ቅርንጫፎችን እንደሚያካትትና ለ17 ዞን፣ 2 ወረዳዎች፣ 1 ከተማ አስተዳደር ስር የሚገኙ 15.6 ሚሊየን በላይ ሕብረተሠብ ክፍሎች እንደሚያገለግል ሥራ አስኪያጁ ተናግረዋል፡፡
በበጀት ዓመቱ በተገላባጭ ፈንድ 319.6 ሚሊየን ብር ወጪ እና በኘሮግራም 3.6 ቢሊየን ብር በላይ ወጪ ያላቸው መድኃኒቶችና የሕክምና መገልገያ መሣሪያዎች ስርጭት እንደተካሄደ የዝግጅት ክፍሉ በሪፖርቱ ተመልክቷል፡፡
በነቀምት ቅርንጫፍ የኢንሲኔሬተር ተከላ መካሄዱ፣ በክላስተሩ መድኃኒቶችን ወደ ጤና ተቋማት በቀጥታ ማድረሣቸው እና መድኃኒቶችን ከቅርንጫፍ ቅርንጫፍ እያዘዋወሩ መጠቀማቸውን ገልፀዋል፡፡
በመጨረሻም በበጀት ዓመቱ የአንዳንድ መድኃኒቶች እጥረት፣ የአገር ውስጥ መድኃኒት አምራቾች መድኃኒት ያለማቅረብ ችግር፣ የፎርክሊፍት እና የመብራት መቆራረጥ ችግሮች እንዳጋጠማቸው አቶ መለስ ተናግረዋል፡፡