የአጎበር ስርጭት ተጠናቀቀ
በግሎባል ፈንድ እና ፒ.ኤስ.ኤም–ፒኤም አይ /በኬሞኒክስ/ ተገዝተው የቀረቡ 15 ነጥብ 8 ሚሊየን አጎበሮች መሠራጨታቸውን የፕሮግራም ስርጭት አስተባባሪ አቶ ሺፈራው በቀለ ከዝግጅት ክፍሉ ጋር በነበራቸው ቆይታ አስታወቁ፡፡
በግሎባል ፈንድ የቀረቡ አጎበሮች ብዛት 10 ነጥብ 3 ሚሊየን በላይ መሆኑን አቶ ሺፈራው ተናግረዋል፡፡
ስርጭቱ በዐማራ እና ኦሮሚያ ክልል በሚገኙ 220 ወረዳዎች መከናወኑን ከአስተባባሪው ገለጻ መረዳት ተችሏል፡፡
በመረጃው 5 ነጥብ 5 ሚሊዮን አጎበሮች በፒ.ኤስ.ኤም–ፒኤም አይ /ኬሞኒክስ/ መቅረቡን አቶ ሺፈራው በላኩት ሰነድ መመልክት ተችሏል፡፡
የፒ.ኤስ.ኤም–ፒኤም አይ /ኬሞኒክስ/ አጎበሮች በደቡብ፣ አፋር፣ ትግራይና በአማራ ክልሎች በሚገኙ 150 ወረዳዎች መሠራጨታቸውን አቶ ሺፈራው ተናግረዋል፡፡
ለኦሮሚያ ከ6 ነጥብ 5 ሚሊዮን በላይ፣ ለዐማራ 4 ነጥብ 6፣ ለትግራይ 564 ሺህ 261፣ ለደቡብ 1 ነጥብ 1 ሚሊየን አጎበሮች ተሠራጭተዋል ተብሏል፡፡
የቀረቡት አጎበሮች ከ729 ነጥብ 9 ሚሊየን ብር በላይ አጠቃላይ ወጪ ወጥቶባቸዋል ሲሉ አስተባብሪው አረጋግጠዋል፡፡
ስርጭቱ ከየካቲት 26 ጀምሮ እስከ ሰኔ ወር 2011 ዓ.ም መጨረሻ ተሰራጭቶ መጠናቀቁን የዝግጅት ክፍሉ መረዳት ችሏል፡፡
ሥርጭቱ ከወደቦች በቀጥታ ወደ ሚፈለግበት ቦታ እንደነበር አቶ ሺፈራው አክለው ተናግረዋል፡፡