የኢትዮጵያ መድኃኒት አቅራቢ ኤጀንሲ የ2012 በጀት አመት የግማሽ አመት እቅድ አፈጻጸም ግምገማውን በአዲስ አበባ እምቢልታ ሆቴል ከየካቲት 8 እና9 /2012 አካሄዷል፡፡
ኤጀንሲው የግዥ ስርዓቱን፡የስርጭት እና ክምችት እንድሁም የፋይናስ አስተዳደሩን መማጠናከር ለጤና አለልግሎቱ የሚያስፈልጉ ጥራታቸው፡ፈዋሽነታቸው እና ደህንነታቸው የተረጋገጡ መሰረታዊ መድኃኒቶች እና የህክምና መገልገያዎችን በበቂ መጠን ፡በተመጣጣኝ ዋጋ እና ቀጣይነት ባለው መልኩ ለማቅረብ በማእከል እና በቅርንጫፎች የተካናወኑትን ጠንካራና ደካማ ጎኖችን የለየበት ለምድ የተለዋወጡበት እና የቀሪ ወራትን የትኩረት ነጥቦች የተቀመጠበት የውውይት መድረክ እንደነበር ተገልጻል፡፡
በዚህም መሰረት 1. በቀጥታ ተጠሪነታቸው ለዋና ዳይሬክተር የሆኑየሰው ሀይል ልማት፡ሪፎርም ናመልካም አስተዳደር፡ኦድት፡ሴቶችና ወጣቶች፡ስነ ምግባር ዳይሬክቶሬቶች ከተከናውኑት ተግባራት በጥቂቱ ስንመለከት
· በዝግጅት ምዕራፍ ከሁሉም ባለድርሻ አካላት ጋር ምክክር ተደርጎ ግብቶች እንደተወሰዱ
· የነጥብ ስራ ምዘና ድልድል ለማድረግ የሰራተኞች መረጃን የማጥራት ስራ እንዲከናወን በማድረግ ምደባውን ለማከናወን የዝግጅት ስራ የተጠናቀቀ ሲሆን ሰራተኞችም ለድልድል መወዳደር ጀምረዋል፡፡ የውድድር ውጤቱም በቅርቡ ይፋ እንደሚሆን ተገልጻል፡፡
· የመድኃኒት አቅርቦት አስተዳደር ምርጥ ተሞከሮ እና የማስተማሪያ የልህቀት ማዕከል (Training Resource Centre) ለማቋቋም የሚስችል ስምምነት የተፈፀመ ሲሆን የማስተማሪያ የልህቀት ማዕከል Business case ተዘጋጅቶ ለማስልጠኛ የሚሆኑ የተመረጡ ካሪኩለሞች በመዘጋጀት ላይ እንደሚገኑ ተገልጻል፡፡
· የሰራተኞች የጥቅማጥቅም መመሪያ ተዘጋጅቶ የቦርዱን የማጽደቅ ውሳኔ እየተጠበቀ እንዳለ ተብራርቷ፡፡
· የኤጀንሲውን አዋጅ መተመለከተ ኤጀንሲውን በአድስ መልክ ለማደራጀት እና የአገልግሎት አሰራሩን ለማሻሻል የዝግጅት መእራፉ ተጠናቆ ቦርዱ አስተያየት ሰጥቶበት የጤና ሚንስቴር የጋራ ስትሪንግ ኮሚቴ ቀርቦ ከጸደቀ በኋላ አዋጅ ሆኖ ለመጽደቅ የሚያስፈልጉትን ቅድመ ሁኔታዎች በመከተል ለጠቅላይ ሚንስቴር ጽ/ቤት ቀርቦ ምላሽ በመጠባበቅ ላይ እንደሚገኝ ተገልጻል፡፡
· ከኤጀንሲው የህዝብ ክንፍ ና ባለድርሻ አካላት ጋር የመልካም አስተዳደር ችግሮችን ለመፍታት ከሙያ ማህበራት ጋር ውይይት እንደተደረገ የጨረታ ውጤት ከተገለጸባቸው 16 ቅሬታዎች በተለያየ ደረጃ ምላሽ እንደተሠጠባቸው እንድሁም 6 የመልካም አስተዳደር ችግሮች ቀርበው ምላሽ ያገኙ እና በሂደት ላይ ያሉ እንዳሉ ተገልጻል፡፡
· የካይዘን ፍልስፍና ትግበራ በሀዋሳ፡መቀሌ ፡ጅማ እና ዋና መ/ቤት በተለያዩ ደረጃ እየተተገበረ እንዳል ታቀውቋል፡፡
· 20 የኦድት ስራዋች በመካናወን ላይ ሲሆኖ ከእነዚህ ውስጥ 7 ቱ ተጠናቀው ሪፖርት ለሚመለከተው አካል መቅረቡ ታውቋል፡፡
· 30 ሴት አስተባባሪዎች በአመራርነት ስልጠና እንዳገኙ እንድሁም ለ 45 ሰራተኞች/28 ቱ ሴት/ በነጻ እና ግማሽ ክፍያ በድግሪ እና ቲቪቲ የትምህርት እድል እንዳገኙ ታውቋል፡፡49 ሴቶች ከቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ጋር መበተባበር የጡት እና የማህጸን በር ካንሰር ምርመራ እንድያደርጉ ተገልጻል፡፡
· የሰራተኞች ስነ ምግባር መመሪያ ክለሳ ፡ የኤጀንሲው እሴቶች አጠቃቀም እና ተግባራዊት ላይ እንድሁም የስነምግባር እና ጸረ ሙስና ጽንሰሀሳብ ዙሪያ ለ 382 ሰራተኞች ስልጠና ተሰጥቶል፡፡
በምክክር ጊዜ ከቀረበው ሰነድ እና ሀሳቦች የነበሩትን አፈጻጸሞች መረዳት የተቻለ ሲሆን የሌሎችን ዘርፎችና ቅርንጫፎችን አፈጻጸሞች ቀጥሎ በቅርብ ቀን የምናቀርብ ይሆናል፡፡
Supply chain of compassion!!!!!
በአወል ሀሰን