ኤጀንሲው ታህሣስ 24 ቀን 2012 ዓ.ም ያስመረቀው የማቀዝቀዣ ሠንሠለት መጋዘን ሥራ ጀመረ፡፡
የኢትዮጵያ መድኃኒት አቅራቢ ኤጀንሲ ታህሣስ 24 ቀን 2012 ዓ.ም ያስመረቀውን 3000 ካሬ ሜትር ስፋት ያለው የቀዝቃዛ ሠንሠለት መጋዘን ከጥር 24 ቀን 2012 ዓ.ም ጀምሮ ሥራ መጀመሩን የቀዝቃዛ ሠንሠለት መጋዘን ኃላፊ አቶ ሚካኤል ዘውገ አስታወቁ፡፡
ማቀዝቀዣ ሠንሠለቶቹ 3 ሲሆኑ እያንዳንዳቸው 300 ሜትር ኪዩብ የመያዝ አቅም እንዳላቸውና ከ2 እስከ 8 ዲግሪ ሴንቲግሬድ ቅዝቃዜ የሚያስፈልጋቸውን የህክምና ግብዓቶች ማከማቸት የሚያስችሉ መሆናቸውን ኃላፊው አብራርተዋል፡፡
በተጨማሪም 2 የከፍተኛ ቀዝቃዛ ክፍሎች/ freezer rooms / እያንዳዳቸው 100ሜ ኩዩብ የመያዝ አቅም ያላቸውና ከ -25 እስከ -15 ድግሪ ሴንቲግሬድ ቅዝቃዜ ለሚያስፈልጋቸው የህክምና ግብዓቶችን ለማከማቸት የሚቻስችሉ ናቸው።
አቶ ሚካኤል የቀዝቃዛ ሠንሠለት መጋዘኑ ሥራ መጀመር ኤጀንሲው የሚያወጣውን ከፍተኛ ወጪ (Demurrage cost) ከማስቀረቱም ባሻገር መድኃኒቶቹ በኤጀንሲው መጋዘን መከማቸታቸው ለጤና ተቋማት በፍጥነት ለማሠራጨት ያስችላል ብለዋል፡፡
የቀዝቃዛ ሠንሠለት መጋዘኑ የተለያዩ ቅዝቃዜ የሚፈልጉ የክትባት መድኃኒቶች፣ የላብራቶሪ መገልገያ ግብዓቶች እና ሌሎች ጥራታቸውን ጠብቀው ለተጠቃሚው ለማድረስ እንዲያስችል ከማድረጉም በላይ በጤናው ዘርፍ የእናቶችና ህጻናት ሞትን ለመቀነስ የተያዘውን እቅድ ለማሳካት የሚያግዝ ነው፡፡