የኤጀንሲው ማነቆዎችን መለየት የመድኃኒት አቅርቦቱን ለማሣለጥ ወሣኝ ሚና እንዳለው ተገለፀ፡፡
በኤጀንሲው ያሉ ማነቆዎችን ለመለየትና መፍትሄ ለማስቀመጥ የሁለት ቀን ወርክሾኘ መካሄዱን በፖሜላ ስቲል አሶሴት ስራ አስኪያጅ የሆኑት ፖም ስቲል አስታወቁ፡፡
ወርክሾፑ በኤጀንሲው ያሉ ማነቆዎችን በጋራ በመለየት የጋራ መፍትሄ ለማስቀመጥና ተልእኮውን ለማሣካት የተዘጋጀ መሆኑን ሥራ አስኪያጇ አስረድተዋል፡፡
በመጀመሪያው ቀን የየዳይሬክቶሬቱን ማነቆዎች በመለየት መፍትሄ ማስቀመጣቸውን ስራ አስኪያጇ ገልፀዋል፡፡
በቀጣይ ቀንም ሁሉም ዳይሬክቶሬቶች የርስ በርስ ማነቆዎች፣ አንዳቸው በአንዳቸው ላይ እንዴት ችግር እንደሚፈጥሩና የጋራ ችግሮቻቸው ላይ ጥልቅ ውይይት ማካሄዳቸውን ተናግረዋል፡፡
ስራ አስኪያጇ በጋራ የጋራና ውጤታማ መፍትሄ አስቀምጠው የተሣለጠ የአቅርቦት ሠንሠለት እንደሚኖር አምናለሁ ሲሉ አስተያየታቸውን ሠጥተዋል፡፡
በቀጣይም በሠው ኃብት፣ በፋይናንስ እና ሌሎች ድጋፍ ሠጪ ዳይሬክቶሬቶች ማነቆዎቹን ለይቶ የመፍትሄ ሃሣብ ወደ ማምጣት ሥራ እንገባለን ብለዋል፡፡
በነበረው የሁለት ቀናት ቆይታ ሁሉም ተሣታፊ ትህትና በተሞላበት መንገድ የራሱን አስተዋጾ ማበርከቱንና የመፍትሔ ሃሣብ ማቅረቡን ተናግረዋል፡፡
ሥራ አስኪያጇ የተሠብሣቢውን አስደናቂ ትህትና፣ ዝግጁነት የልምድና የእውቀት ማጋራት እና ለአቅርቦት ሠንሠለቱ መሣለጥ የቀየሱትን አዳዲስ ዘዴዎች አድንቀዋል፡፡
በወርክሾፑ የግዢ ትንበያና ገበያ ጥናት፣ የስርጭትና የተሽከርካሪ ስምሪት፣ የጨረታ አስተዳደር፣ የኮንትራት አስተዳደር እና የክምችት እና የመጋዘን አስተዳደርዳይሬክቶሬት ሠራተኞች መሣተፋቸውንና ለአቅርቦት ሠንሠለቱ መሣለጥም ዋንኛ ክፍሎች ናቸው ሲሉ ፖም ስቲል አብራርተዋል፡፡
በአምስቱም ዳይሬክቶሬቶች ቅድሚያ ሊሠጣቸውና በቀጣይ 3 ወራት ሊፈቱና ሊተገበሩ የሚገባቸውን ማነቆዎች እንደለዩ በወርክሾፑ አድምጠናል፡፡
ወርክሾፑ ከነሐሴ 11-12/2011ዓ.ም. በአዳማ ከተማ መካሄዱን የዝግጅት ክፍሉ ተመልክቷል፡፡