የኤጀንሲው የመድሃኒት ግዥ መዘርዝሩን ክለሳ ተጀመረ::
የኢትዮጵያ መድሃኒት አቅራቢ ኤጀንሲ ከአሁን በፊት በ ሚያዚያ 2018 የተዘጋጀውና አስከ አሁን ጥቅም ላይ የዋለው እንዲሁም በየሁለት ዓመቱ እንዲከለስ የሚጠበቀው የኤጀንሲው የመድኃኒት ግዥ መዘርዝር/ pharmaceuticals procurement list/ መከለስ ተጀመረ፡፡
ከኤጀንሲውና ከጤና ሚኒስቴር የተወጣጡ የሚመለከታቸው ባለሙያዎች ያሉትን ጠንካራ እና ደካማ ጎኖች በመለየት በዜሮ ድራፍት ደረጃ የማዘጋጀት ስራ የተጀመረ ሲሆን በቀጣይ ከጤና ተቋማት እና ከባለድርሻ አካላት ጋር በስፋት በውይይት ዳብሮ አገራዊ ይዘት እንድኖረው ይደረጋል፡፡
ክለሳው ከሶስት አመት በፊት ያለውን አገራዊ እና የጤና ተቋማትን የፍጀታ መረጃዎች፣ ከአሁን በፊት በነበረው ዝርዝር ላይ የሌሉ ነገር ግን በጤና ተቋማት እጅግ ተፈላጊ የሆኑ መሰረታዊ እና አስፈላጊ የሆኑ/vital/ የህክምና ግብዓቶች እና ሌሎች መዘርዝሩን ለማዘጋጀት ታሳቢ ያደረጋቸው ሲሆኑ በአዲስ መልክ በሌላ የተተኩ እና በብዛት ተፈላጊ ያልሆኑ/Old molecules/ በአድሱ ዝርዝር እንዲካተቱ አይደረግም፡፡ በተጨማሪም አዲሱ የመድሃኒት መዘርዝር የሀገሪቱን የኢኮኖሚ አቅም እንዲሁም የህብረተሰቡን የመግዛት አቅም ያማከለ በግል ለመግዛት ውድ የሆኑትን ያካተተ እና የተመጠነ እንዲሆን ይደረጋል፡፡Supply chain of compassion!!!