የጤና አገልግሎት ተደራሽነትን እና ጥራትን ለማረጋገጥ በድጅታል ቴክኖሎጂ የታቀፈ የተቀናጀ የአሰራር ስርዓት ስራ ላይ ማዋል ተገቢ መሆኑ ተገለጸ፡፡
የጤና አገልግሎት ተደራሽነትን እና ጥራትን ለማረጋገጥ በድጅታል ቴክኖሎጂ የታቀፈ የተቀናጀ የአሰራር ስርዓትን ስራ ላይ ማዋል ተገቢ መሆኑን የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ምክትል አፈጉባኤ የተከበሩ ሎሚ በዶ ገለጹ፡፡
የኢትዮጵያ መድኃኒት አቅራቢ አገልግሎት የመድሃኒት አቅርቦት ስርዓቱን ድጅታላይዝ በማድረግ በቅርቡ ስራ ላይ በሚያውለው የተቀናጀ የመረጃ ስርአት (Enterprise Resource Planning ERP )ትግበራ ሂደት አስመልክቶ ከፓርራማ አባላት ጋር ሚያዚያ 12 ቀን 2016 ዓ.ም ውይይት አድርጓል፡፡
በመድረኩ በክብር እንግድነት የተገኙት የምክር ቤቱ ምክትል አፈ ጉባዔ የተከበሩ ወ/ሮ ሎሚ በዶ እንደተናገሩት የኢትዮጵያ መድሃኒት አቅራቢ አገልግሎት የአቅርቦት ስርዓቱን ለማዘመን ቀልጣፋ እና ግልፅ እንዲሆን ለማስቻል (ERP) የተቀናጀ መረጃ ስርአት ትግበራ በህግ ለማስደገፍ ለተጀመረው ሂደት መድረኩ ትልቅ ፋይዳ እንደሚኖረው ገልፀዋል።
ድጅታል ኢትዮጵያን መነሻ በማድረግ የኢትዮጵያ መድኃኒት አቅራቢ አገልግሎት አሰራሩን በቴክኖሎጅ በማዘመን የህክምና ግብአቶች አቅርቦቱን የተቀናጀ፤ቀልጣፋ ግልጽ እና ተጠያቂነት የሰፈነበት ለማድረግ እየተሰሩ ያሉትን ስራዎች ሁሉም አካል ሊደግፍ እንደሚገባ ምክትል አፈጉባኤዋ ተናግረዋል፡፡
ለማህበራዊ ፡ኢኮኖሚያዊ ፖለቲካዊ ጉዳዮቻችን ጤና መሰረት በመሆኑ ጤናማ ዜጋ ለመፍጠር የኢትዮጵያ መድኃኒት አቅራቢ አገልግሎት ሊደር ሽፕ ከላይ እስከታች ተቀናጅቶ እየተሰሩ ያሉ ብዙ ስራዎች መኖራቸውን አድንቀው ከህዝቡ የመድሃኒት ፍላጎት እርካታ እንዲሁም ከተቋሙ ውስጥ እና ውጭ ባሉ ችግርች አኳያ ሲታይ የሚቀሩ ስራዎች መኖራቸውን አብራርተዋል፡፡
የዜጎችን ጤና ማስጠበቅ ያስችል ዘንድ የዚህ የአሠራር ሥርዓት መዘርጋት ጉልህ ሚና እንደሚኖረው አፈ ጉባዔዋ ጠቁመው፤ የባለድርሻ አካላት ማለትም ኢትዮ ቴሌኮም፣ የኢንፎርሜሽን ደህንነት አስተዳደር፣ አርቲፌሻል ኢንተለጀንስ እና ሌሎችም የሚመለከታቸው አስፈፃሚ አካላት አስፈላጊውን ድጋፍ ማድረግ ይኖርባቸዋል ሲሉ ተናግረዋል።
ተቋሙ የጀመራቸውን የለውጥ ሥራዎች ማስተግበሪያ የሚሆን የአገልግሎቱ እንደገና ማቋቋሚያ አዋጅ ቶሎ ወደ ፓርላማ መጥቶ ጠቃሚ ግብአቶች ተካተው ይህን ቴክኖሎጅ ሊያሰራ በሚችል አዋጅ መጽደቅ አለበት ሲሉ ም/ አፈጉባኤዋ አብራርተዋል፡፡
በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የጤና፣ ማህበራዊ፣ ባህልና ስፖርት ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ የተከበሩ ወ/ሮ ወርቀሰሙ ማሞ በሀገራችን የጤና ፖሊሲው መከላከል ላይ ቢያተኩርም ህሙማንን ከሞት ለመታደግ የመድሀኒት አቅራቢ አገልግሎት አሰራሩን ለማዘመን የጀመረው ከድጅታል ኢትዮጵያ ከዚያም ድጅታ ል ሄልዝ ትግበራ ተቋሙን ውጤታማ ስለሚያደርገው ባለድርሻ አካላት በቅንጅት ሊደገፉት ይገባል ሲሉ ገልፀዋል።
የተለያዩ አማራጮች ቀርበው በፓይለት አንዱ ከሌላው ትምህርት እየተወሰደበት የድጅታል ስርኣቱን ለመተግበር መወሰኑ መልካም ነው ሲሉ አክለዋል፡፡
ምናልባትም ከሮኬት ሳይንስ ቀጥሎ የመድኃኒት አቅርቦት ሰንሰለት ውስብስብ ነው ያሉት የኢትዮጵያ መድኃኒት አቅራቢ አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር አብዱልቃድር ገልገሎ “ERP –SAP” የተባለውን ቴክኖሎጅ ከአየር መንገድ፤ኢትዮ ቴሌኮም፡ሽፒንግ ላይን እና ባንኮች ቀጥለን ስራ ላይ ስናውል ልምድ ከማገኘታችን ባሻገር እሴት የማይጨምሩ አሰራሮችን በመለየት እንዲቀሩ ተደርጓል ብለዋል፡፡
ዋና ዳይሬክተሩ ዶ/ር አበዱልቃድር EPSS ያለበትን አሁናዊ ቁመና የሚያሣይ ገላጭ የመነሻ ጽሑፍ ያቀረቡ ሲሆን፤ ዲጂታል ሄልዝ በሚል ቀድመን ከምንስራበት “Vitas” ወደ “ERP” የተቀናጀ የመረጃ ስርአት አሁን ላይ የሲስተም ፍተሻዉ ተጠናቆ ደንበኞችን ማስተናገድ የሚጀምርበት ደረጃ ላይ መድረሱን እና በመጭው ግንቦት ወር ላይ በይፋ ስራ ላይ (Go Live )እንደሚውል ተናግረዋል።ሲስተሙ ተግባራዊ ሲሆን በመድሃኒት ክምችትና ሥርጭት ወቅት የሚያጋጥሙ ብልሹ አሰራሮችን በማስቀረት በመድሀኒት እጦት የሚሰቃዩ ወገኖችን መታደግ ያስችለናል ብለዋል።
ለተቋሙ መድኃኒትን የማቅረብ ትልቅ ስራ ተሰጥቶት ራሱ ነጻ መሆን ይቀረዋል( Too much mandate with limited autonomous) ይህም በቴክኖሎጅ ታግዘን በጥብቅ የስራ ድስፕሊን በቀጥታ መድሃኒት ቶሎ ቶሎ ወደ ታካሚዎች ለማድረስ ያሉ ማነቆች በትብብር ልነፈታቸው ይገባል ብለዋል፡፡
በ958 የመፍትሄ እና የመሰረተ ልማት የትግበራ ሙከራ ተደርጎ 3 ቱ ላይ ብቻ እጥረቶች በመታየታቸው ሙከራውን ባላለፉት ላይ ትኩረት ተደርጎ ተሰርቷል ያሉት የኢትዮጵያ መድኃኒት አቅራቢ አገልግሎት ም/ ዋና ዳይሬክተር አቶ አቅናው ካውዛ ከ9 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር ለፕሮጃክቱ መመደቡን አብራርተዋል፡፡
በመጨረሻም ዋና ዳይሬክተሩ ላቀረቡት ማራኪ የማወያያ ጹሁፍ የፓርላማ አባላቱ ያመሰገኑ ሲሆን በዲጂታል ሲስተም ትግበራው ሂደት የሚያጋጥሙ የሲስተም ድህንነት እና ተያያዥ ችግሮችን በምን መልኩ መፍታት እንደሚችሉ እና ምን አይነት ቅድመ ዝግጅቶችን ማድረግ እንደሚገባቸው ከተሣታፊዎች አስተያየትና ምክረ ሀሳብ ተሰንዝሯል፡፡
#ማገልገል ክብር ነው!!!
አወል ሀሰን