የ2016 የህክምና ግብቶች ቆጠራ በበቂ ቅድመ ዝግጅት የ”ERP _ SAP”ን ቴክኖሎጅ መሰረት ባደረገ መልኩ የሚካሄድ መሆኑ ተገለፀ።
የኢትዮጵያ መድኃኒት አቅራቢ አገልግሎት የERP ቴክኖሎጂ አካል የሆነውን SAP ለመተግበር አስፈላጊ ቅድመ ዝግጅቶች ተጠናበው የ2016 ለቆጠራ የERP ቴክኖሎጂ SAP መሰረት ባደረገ መልኩ እንደሚካሄድ የኢትዮጵያ መድኃኒት አቅራቢ አገልሎት ም/ ዋና ዳይሬክተር አቶ ታሪኩ በላቸው ገለፁ።
ቆጠራውን ለሚያስተባብሩ እና ለሚቆጥሩ ሙያተኞች የቅድመ ቆጠራ ኦሬንቴሽን ሰሞኑን ተሠጥቷል።
የህክምና ግብአቶች አመታዊ ቆጠራ ሲደረግ በከፍተኛ የሀላፊነት ስሜት እና በጥንቃቄ መሆን እንዳለበት አቶ ታሪኩ መልዕክት አስተላልፈዋል።
አዲሱን የተቀናጀ የመረጃ ስርዓት ስራ ላይ ለማዋል በርካተ ስራዎች የተሠሩ ሲሆን ከእነዚህም መካከል የኮማንድ ሴንተር ማቋቋም ፣ ማስተር ዳታ ትክክለኝነትና ጥራትን ማረጋገጥ ፣ የህክምና የግብዓት ስርጭት ማድረግ ፣ ለባለሙያዎች ስልጠና መስጠት ፣ ቅድመ ቆጠራ ዝግጅት ማድረግ እና የኮሚኒኬሽን ስራዎችን መስራት ከተከናወኑት ተግባራት ውስጥ በዋናነት ይጠቀሳሉ ።
አሁን ላይ እየተከናወነ የሚገኘው የቅድመ ቆጠራ ዝግጅት ሲሆን ቆጠራውን መጋዘን ውስጥ የሚከናወኑ ቅድመ ቆጠራ ዝግጅት በተጨማሪ አዲሱን የመረጃ ስርዓት (ERP/SAP) መሰረት ባደረገ መልኩ የሚያገለግለው ቴፕሌት በርካታ ዝርዝር መረጃዎችን የሚይዝ በመሆኑ እና የቆጠራውን ፍጥነትና ውጤታማነት የሚያሳድግ የኮምፒውተር ፕሮግራም የአዳማ ቅርንጫፍ አይ.ቲ (IT) ባለሙያ አቶ በየነ ዳባ ተዘጋጅቷል ፡፡
የተዘጋጀው የኮምፒውተር ፕሮግራም ለሁሉም የቅርንጫፍ መጋዘን ሀላፊዎች አና ባለሙያዎች ፕሮግራሙን የማስተዋወቅ እንዲሁም የሙከራ ቆጠራ ተከናውኗል ፤ የተዘጋጀው የኮምፒውተር ፕሮግራም በቆጠራው ላይ ከፍተኛ አስተዋፅኦ እንደሚያበረክት ተጠቅሶ ፤ በሙከራው ወቅት የገጠማቸውን ተግዳሮቶች የአገልግሎቱ ከፍተኛ አመራሮች በተገኙበት ለውይይት ቀርቧል ።
በአጠቃላይ ቅድመ ቆጠራ ዝግጅት ላይ ተከናወኑ ያሉ በርካታ ስራዎችን ማጠናቀቅና ለቆጠራ እግጁ መሆን አስፈላጊ መሆኑን የአገልግሎቱ ዋና ዳይሬክተር ገልፀው ፤ ሁሉም ባለሙያዎች ERP ቴክኖሎጂን ለመተግብር ላሳዩት ተነሳሽነትና ተሳትፎ ምስጋናቸውን አቅርበዋል ፡፡