የኢትዮጵያ መድኃኒት አቅራቢ ኤጀንሲ ከGHSC-PSM /ኬሞኒክስ/ ጋር በመተባበር 3.1 ሚሊየን አጎበሮችን ለ3 ክልሎች ስርጭት መጀመሩን የመድኃኒትና የሕክምና መገልገያዎች ስርጭትና ተሽከርካሪ ስምሪት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ አሕመድ ከድር ጥር 27 ቀን 2012 ዓ.ም. ገለፁ፡፡ ኤጀንሲው ከ3 ዓመት በፊት የተሠራጩትን አጎበሮች ቅያሪ እያካሄደ እንደሆነና አንድ አጎበር ለ3 ዓመት ብቻ የሚያገለግልና አጎበር ላይ የሚረጨው ኬሚካል ከ3 ዓመት በላይ […]