የኢትዮጵያ መድኃኒት አቅራቢ ኤጀንሲ ታህሣስ 24 ቀን 2012 ዓ.ም ያስመረቀውን 3000 ካሬ ሜትር ስፋት ያለው የቀዝቃዛ ሠንሠለት መጋዘን ከጥር 24 ቀን 2012 ዓ.ም ጀምሮ ሥራ መጀመሩን የቀዝቃዛ ሠንሠለት መጋዘን ኃላፊ አቶ ሚካኤል ዘውገ አስታወቁ፡፡ ማቀዝቀዣ ሠንሠለቶቹ 3 ሲሆኑ እያንዳንዳቸው 300 ሜትር ኪዩብ የመያዝ አቅም እንዳላቸውና ከ2 እስከ 8 ዲግሪ ሴንቲግሬድ ቅዝቃዜ የሚያስፈልጋቸውን የህክምና ግብዓቶች ማከማቸት […]