ኤጀንሲው ፌታል ሞኒተር (fetal monitor) የተሠኘ የፅንስ ጤንነት መከታተያ የሕክምና መገልገያ መሣሪያ እያሰራጨ መሆኑን የሕክምና መሣሪያዎች ስርጭት ኦፊሠር አቶ ጂአ ኡጋ ገለፁ፡፡ የሕክምና መገልገያ መሣሪያው ለፅንስ ጤንነት መከታተያ አገልግሎት እንደሚውልና ስርጭቱ ለ27 ሆስፒታሎች እየተካሄደ እንደሚገኝ ኦፊሰሩ አስረድተዋል፡፡ እንደ አቶ ጂአ ገለጻ የሕክምና መገልገያ መሣሪያው ብዛቱ 140 እንደሆነና ከ5 ሚሊየን ብር በላይ ወጪ እንዳለው ታውቋል፡፡