የኢትዮጵያ መድኃኒት አቅራቢ ኤጀንሲ የአዳማ ፕሮጀክት ለራጅ ምርመራ አገልግሎት የሚውሉ 25 የኤክስሬ ማሽኖችን እያሰራጨ መሆኑን የህክምና መሳሪያዎች ስርጭት ባለሞያ አቶ ሀይማኖት ጌታሁን ተናገሩ፡፡ ስርጭቱም በአዳማ ፕሮጀክት አማካኝነት ለኦሮሚያ፣ለአማራ፣ለአፋር፣ለቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልሎች የተሰራጩ ሲሆን በአጠቃላይ 16 የኤክስሬ ማሽኖች መሰራጨታቸውን አቶ ሀይማኖት አስታውቀዋል፡፡ በቀጣይ ለሶማሌ፣ለትግራይ፣ለደቡብ ብሔር ብሔረሰቦችና ህዝቦች ክልሎች ስርጭት የሚካሄድ ሲሆን አጠቃላይ 138 ሚሊዮን 72 ሺህ 448 […]