የኢትዮጵያ መድኃኒት አቅራቢ አገልግሎት ድርቅ ለተከሰተባቸው ዞኖች ከ15 ሚሊየን በላይ ዋጋ ያላቸው ግብዓቶችን ማሰራጨቱን የመደበኛ ፕሮግራም ክምችት ባለሙያ አቶ አገኘሁ ናደው የካቲት 30 ቀን 2014 ዓ.ም አስታወቁ፡፡ የተሰራጩት ግብዓቶችም በዞኖች ከተከሰተው ድርቅ ጋር ተያይዞ ለሚከሰቱ የተለያዩ በሽታዎችን ለመከላከልና ለመቆጣተር የሚያስችሉ የተለያዩ መድኃኒቶች ፣የህፃናት አልሚ ምግቦች እንዲሁም ውሃ ወለድ በሽታዎችን ማከሚያ መድኃኒቶች መሆናቸውን ባለሙያው አብራርተዋል፡፡ ከተሰራጩት […]