የኢትዮጵያ መድኃኒት አቅራቢ አገልግሎት የአዳማ ቅርንጫፍ በ2014 በጀት ዓመት በቅርንጫፉ ለተመዘገቡ በርካታ ክንውኖች ከፍተኛ አስተዋፅኦ ላበረከቱ ሠራተኞች የእውቅና እና የምስጋና ምስክር ወረቀት መስከረም 28 ቀን 2015 ዓ.ም ተሰጠ። የዋና ዳይሬክተር ፅህፈት ቤት ሀላፊ አቶ እንግዳየሁ ደቀባ በመረሃ ግብሩ ተገኝተው ባደረጉት ንግግር የአዳማ ቅርንጫፍ የላቀ የስራ አፈጻጸም በማስመዝገብ በግንባር ቀደምትነት ከሚጠቀሱት ቅርንጫፎች አንዱ እንደሆነና ለሌሎችም አርአያ […]