58 አይነት የኬሚስትሪ መመርመሪያ ሪኤጀንቶች ተሰራጩ፡፡
April 11, 2022News
የኢትዮጵያ መድኃኒት አቅራቢ አገልግሎት በፕሌስመንት ግዥ ያስገባቸውን 58 አይነት ሪኤጀንቶች ከመጋቢት 12 እስከ 23 ቀን 2014 ዓ.ም ማሰራጨቱን የመድኃኒትና ክምችት ባለሙያ አቶ ብሩክ ክፍሌ ገለጹ፡፡ የተሰራጩት የdimension DXL200 ሪኤጀንቶች ሲሆኑ ለጉበት ፣ለኩላሊት፣ለኮልስትሮልና ለኤሌክትሮ ላይት ምርመራ አገልግሎት እንደሚውሉ አቶ ብሩክ ተናግረዋል፡፡ስርጭቱም በደሴ፣ በባህርዳር፣ በአርባ ምንጭ፣ በጅማ፣ በሰመራና በሀዋሳ ቅርንጫፎች አማካኝነት ለደቡብ ብሔር ብሔረሰቦችና ህዝቦች፣ ለአማራ፣ ለኦሮሚያና ለአፋር ክልሎች ሲሆን 43 ሚሊየን 139 ሺህ 158 ብር ወጪ ተደርጎበታል፡፡
ሂሩት ኃይሉ