የBeckman coulter ክልኒካል ኬሚስትሪ ሪኤጀንቶች መሰራጨታቸው ተገለጸ
December 22, 2021Featured News
የኢትዮጵያ መድኃኒት አቅራቢ አገልግሎት በፕሌስመንት የገዛቸውን የbeckman coulter ክልኒካል ኬሚስትሪ ሪኤጀንቶች ለጥቁር አንበሣ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታልና ለጎንደር ዩንቨርስቲ ሆስፒታል ማሠራጨቱን የመድኃኒትና የክምችት ባለሙያ አቶ ብሩክ ክፍሌ ታህሳስ 7 ቀን 2014 ዓ. ም አስታወቁ፡፡የሪኤጀቶቹ ስርጭትም ከህዳር 25 እስከ 27 ቀን 2014 ዓ .ም በአገልግሎቱ ቅርንጫፎች አማካኝነት ለሆስፒታሎቹ የተካሄደ መሆኑን ባለሙያው ገልጸዋል፡፡ ሪኤጀንቶቹ ለክልኒካል ኬሚስትሪ ምርመራ ለማካሄድ የሚያገለግሉ ሲሆን 22 ሚሊየን 82 ሺህ 14 ብር ወጪ ተደርጎባቸዋል፡፡
ሂሩት ኃይሉ