ተቀናጅቶ ለመስራት ቁርጠኛ መሆናቸውን ባለድርሻ አካላት ገለፁ፡፡
የኢትዮጵያ መድኃኒት አቅራቢ አገልግሎት የክትባት መድኃኒቶችንም ሆነ ሌሎች የህክምና ግብዓቶችን ገዝቶ በማስገባት፣ በማከማቸትም ሆነ በስርጭት ሂደት የባለደርሻ አካላት ቅንጅት ለስራው ቁልፍ መሆኑ ከአዳማ ከተማ በተደረገ የምክክር ወርክሾፕ ተገልጿል፡፡የክትባት መድኃኒቶችን በግዥ እንዲያቀብለን ለዩኒሴፍ ውክልና ተሰጥቶ የኢትዮጵያ መድኃኒት አቅራቢ አገልግሎት በመረከብ የማከማቸትና የማሰራጨት ስራ ይሰራል ያሉት ለጤና ሚኒስቴር የእናቶች ፣ ህፃናት ዳይሬክቶሬት ረዳት ዳይሬክተር እና የብሄራዊ ክትባት አስተባባሪ የሆኑት አቶ ዮሀንስ ላቀው የተናገሩ ሲሆን ክትባቶች በተቀመጠው በ72 ሰዓት ጊዜ ውስጥ ከትራንስፖርት ተቋማት የማይላቀቁ /Clear/ የማይደረጉ ከሆነ ብልሽት ያጋጥማቸዋል የሚል ስጋት እንዳላቸው ተናግረዋል፡፡የግንዛቤ እጥረት፣ የመረጃ ልውውጥ እንዲሁም ከስራ ውክልና ጋር የሚያያዙ ችግሮች በከፍተኛ ወጪ ተገዝተው የሚመጡ ክትባቶችን በወቅቱ እንዳይጓጓዙ እያደረገ ነው ብለዋል፡፡33 ሚሊዮን ዶዝ የሚሆን የኮሮና ክትባት በተቀናጀ መልኩ ስርጭት እንደተደረገ አስታውሰው ጥናቶች እንደሚያሳዩት” ክትባቶች ከንፁህ መጠጥ ውሃ ቀጥሎ በአለም ላይ በሽታዎችን የምንከላከልባቸው መንገዶች በመሆናቸው ትልቅ ጥንቃቄ ያስፈልጋቸዋል” ሲሉ ገልፀዋል፡፡ የኢትዮጵያ መድኃኒት አቅራቢ አገልግሎት የአየር መንገድ ቁልፍ ደንበኛ በመሆኑ የጭነት ዋጋ ሲተመን የመጡት ግብዓቶች ለህብረተሰቡ የሚሰጡት አገልግሎት ግምት ውስጥ ይገባል ያሉት የኢትዮጵያ አየር መንገድ የካርጎ ክፍል የህክምና ግብዓቶች የሎጀስቲክስ ክፍል ሀላፊው አቶ ብስራት ገ/ማሪያም በአሁኑ ወቅት አየር መንገዱ ከየትኛውም የአለም ክፍል በ18 ሰዓት ውስጥ ጭነቶችን የማጓጓዝ አቅም ገንብቷል ብለዋል፡፡490 ሚሊዮን ዶዝ የኮቪድ-19 ክትባት ለ37 ሀገሮች እንዲጓጓዙ የተናገሩት አቶ ብስራት የጭነት፣ የመጋዘን ዋጋ ጭማሪ አውሮፕላኖቹ እጅግ ዘመናዊ በመሆናቸው ከሚጠቀሙት ነዳጅና ቴክኖሎጂ ጋር የመጣ ነው ብለዋል፡፡ሆኖም ግን ማህበራዊ ሀላፊነት ስላለብን በተቻለ አቅም ለህዝባችን መድኃኒት ለማቅረብ በጋራ እንሰራለን ሲሉ ገልፀዋል፡፡ ለሚፈጠሩ ችግሮች ከመፈጠራቸው በፊት የቴክኒክ ቡድን ተቋቁሞ በየጊዜው እየተፈቱ መሄድ አለባቸው ያሉት በኢትዮጵያ ምግብና መድኃኒት ቁጥጥር ባለ ስልጣን የመአከላዊ ኢትዮጵያ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ ሲሆኑ ከሰዎች ቅንነት መጓደል ወይም ከቁርጠኝነት ማነስ ጋር የሚስተዋሉ ችግሮች አይኖሩም ማለት እንደሆነ ተናግረዋል፡፡ሁለቱ እህትማማች ተቋማት አንዱ ገዥ ሌላው ተቆጣጣሪ ቢሆኑም በጋራ የሚሰሯቸው ጉዳዮች ብዙ በመሆናቸው በትብብር ለመስራት ዝግጁነታቸውን ገልፀዋል፡፡
አወል ሀሰን