ከጤና ሚንስቴር በድጋፍ የተገኙ በጦርነቱ ጉዳት የደረሰባቸውን ጤና ተቋማት መልሶ ለማቋቋም የሚውሉ የተለያዩ የህክምና መሳሪያዎች በአገልግሎት ተቋሙ በኩል መሰራጨታቸው ተገለጸ
April 18, 2022News
የኢትዮጵያ መድኃኒት አቅራቢ አገልግሎት በአማራና አፋር ክልሎች በጦርነቱ የወደሙ ጤና ተቋማትን መልሶ ለማቋቋምና የተሟላ አገልግሎት እንዲሰጡ ለማስቻል ከጤና ሚንስቴር በድጋፍ የተገኙ ከ70 አይነት በላይ የህክምና መሳሪያዎችን ከመጋቢት 22 ቀን 2014 ዓ.ም ጀምሮ ማሰራጨቱን የባዮ ሜድካል ኢንጅነር የሆኑት አቶ የቻለ ሽፈራው ገለጹ፡፡ከተሰራጩት የህክምና መሳሪያዎች መካከል ICU-bed, Oxygen concentrator, ECG Machine, Sterilizer, Monitor-Patient, Mechanical Ventilator, Couch-Delivery, Microscope-Binocular, Neonatal bed እና Examination Table በዋናነት ተጠቃሽ ናቸው፡፡ስርጭቱም በአዲስ አበባ ቁጥር 2፣ በደሴ፣በሰመራ፣በጎንደርና በባህርዳር ቅርንጫፎች አማካኝነት 36 ለሚሆኑ ጤና ተቋማት የተካሄደ ሲሆን ከ150 ሚሊየን ብር በላይ ወጪ ተደርጎባቸዋል፡፡ ከጤና ተቋማቱ መካከል ደሴ ሪፈራል፣ ቦሩሜዳ፣ ወልዲያ፣ ከልዋን፣አምደወርቅ፣ ወልቃይት፣ ቆቦ፣ ኮምቦልቻና ላሊበላ ሆስፒታሎች ለአብነት ተጠቃሽ መሆናቸውን ባለሙያ ተናግረዋል፡፡
ሂሩት ኃይሉ