የአመራርነት ክህሎት ስልጠና ያጠናቀቁ 54 የአገልግሎቱ አመራሮች የምስክር ወረቀት ተሰጣቸው።
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨
የኢትዮጵያ መድኃኒት አቅራቢ አገልግሎት የ10 አመት ስትራቴጂክ እቅድ ለመተግበር ካስቀመጣቸው እቅዶች አንዱ የአመራሩን የመፈፀም አቅም ማጎልበት ሲሆን (Your Transformational Challenge YTC STEP 2.0) የዚህ አካል የሆነውን ለተከታታይ 6 ወራት በተለያዩ ርዕሰ ጉዳዮች የተሰጠውን ስልጠና የወሰዱ 54 አመራሮች በታህሳስ ወር 2016 ዓ.ም ስካይ ላይት ሆቴል በተደረገ ስነ-ስርዓት የምስክር ወረቀት አግኝተዋል ።
የኢትዮጵያ መድኃኒት አቅራቢ አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር አብዱልቃድር ገልገሎ ለተመራቂዎች እንኳን ደስ ያላችሁ መልክት ያስተላለፉ ሲሆን፤ ዛሬ የተሰጣችሁ የምስክር ወረቀት የመጨረሻችሁ ሳይሆን የአዲስ ምዕራፍ መጀመሪያ ሆኖ የሚያገልግል ነው ብለው ለስልጠናው መሳካት ጤና ሚኒስቴር፣ ሮስቴክ ኢምፓወር ኮንሰልቲንግ በተለይም ግሎባል ፈንድ ላደረጉት የገንዘብና የቴክኒክ ድጋፍ ምስጋና አቅርበዋል፡፡
ዶ/ር አብዱልቃድር አክለውም በደቡብ አፍሪካ፣ ኡጋንዳ እና ዛምቢያ ካሉ ተመሳሳይ የመድኃኒት አቅርቦት ሰንሰለት ተቋማት ለ24 አመራሮች እውቀት እና የልምድ ልውውጥ እንዲያገኙ መደረጉ ለህዝቡ የህክምና ግብአቶችን በማቅረብ ሂደት የሚያጋጥሙን ፈተናዎች በቀላሉ ለመፍታት ያግዛል፤ ስለሆነም የወሰድናቸውን እውቀትና ልምዶች ወደ ተግባር በመለወጥ የአቀርቦት ሰንሰለቱ እንዲሻሻል መስራት ይኖርችኋል ሲሉ አሳስበዋል ፡፡
እኛ አፍሪካውያን በፓን አፍሪካኒዝም እሳቤ በመሰባሰብ የሚያጋጥሙን ችግሮች በጋራ በመፍታት ለውጥ ማምጣት አለብን በዚህም በእለቱ የተመረቁት አመራሮች አገልግሎቱን ወደ ተሻለ የአቅርቦት ሰንሰለት ማሻገር እንደሚችሉ የሮስቴክ ኢንፓወርመንት ኮንሰልቲንግ ዋና ስራ አስፈፃሚ ፊሊፕ ካኩሩ እምነታቸው መሆኑን ገልፀዋል።
#ማገልገል ክብር ነው።