በ3 ወራት ጊዜ መፈታት የሚገባቸው ማነቆዎች መለየታቸው ተገለፀ፡፡
August 29, 2019ፊውቸርድ ዜና
በግዥ ትንበያና ገበያ ጥናት ዳይሬክቶሬት 17 ማነቆዎች መለየቱን የኤች. አይቪ፣ ቲቢ እና ወባ ግብዓቶች ግዥ ትንበያ ቡድን መሪ ወ/ት ፅዮን ፀጋዬ ለዝግጅት ክፍሉ ተናገሩ፡፡
በቀጣይ 3 ወራት ውስጥ ሊሠሩ የሚገቡ አንገብጋቢ ማነቆዎችን እና መፍትሔ ለማበጀት መለየታቸውን ቡድን መሪዋ ገልፀዋል፡፡
የገበያ ጥናት ሥራ አለመሥራት፣ የጤና ተቋማት የሚያቀርቡት የግዥ ትንበያ እና ያላቸው በጀት አለመመጣጠን እንዲሁም ከግዥ ጋር በተገናኘ የአቅርቦት እቅድ፣ የግዥ ጥያቄና ትክክለኛ የማስረከቢያ ጊዜ ያለመጣጣም ችግሮች በ3 ወራት ጊዜ ቅድሚያ እንዲፈቱ ለይተናል ብለዋል፡፡
የጤና ተቋማት ግዥ ትንበያ ላይ ያላቸው ተሣትፎ ዝቅተኛ መሆን፣ በተለያዩ አካላት ላይ የዝግጁነት ችግር መኖር፣ የመረጃ ጥራትና አያያዝ ችግር፣ የመድኃኒት መዘርዝራችን ከሌሎች ባለድርሻ አካላት ጋር አለመመሣሠሉ በዳይሬክቶሬቱ በዋነኛ ማነቆነት መለየታቸውን አስታውቀዋል፡፡
በአዳማ በተካሄደው የ2 ቀን ወርክ ሾኘ ላይም አንዱ ከሌላው ምን እንደሚፈልግ መለየቱንና መፍትሔዎችን አስቀምጠናል ብለዋል፡፡
ወ/ት ፅዮን በዳይሬክቶሬታቸው ስር 5 ቡድኖች መኖራቸውንና በየቡድኑ ያሉትን ማነቆዎችም በጋራ መለየታቸውን ገልፀዋል፡፡