የስዊዲን ባለስልጣናትና ባለሀብቶች ኤጀንሲውን ጎበኙ፡፡
November 11, 2019ፊውቸርድ ዜና
ከስዊዲን የመጡ ልዑካን ቡድን ጥቅምት 26 ቀን 2012 ዓ.ም. የኢትዮጵያ መድኃኒት አቅራቢ ኤጀንሲን ጎበኙ፡፡
የልዑካን ቡድኑ በስዊዲን የጤና ሚኒስቴሯ ሊና ሃሌንግሬ የሚመራ ሲሆን የስዊዲን የመንግስት ኃላፊዎች እና አለም አቀፍ የመድኃኒት አምራች ኩባንያዎች ተገኝተው ኤጀንሲውን ጎብኝተዋል፡፡
ስዊዲን ከቀዳማዊ ኃይለሥላሴ ዘመን አንስቶ ከኢትዮጵያ ጋር ግንኙነት እንዳላትና አሁንም የጤና ሴክተሩን ግንኙነትና ኢንቨስትመንቱን ለማጠናከር መምጣታቸውን በስዊዲን ኤምባሲ አስተባባሪ አቶ ሙራድ አብዱራሂድ ተናግረዋል፡፡
የኤጀንሲው ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ተስፋለም አድራሮ ለልዑካን ቡድኑ የኤጀንሲውን ተግባር እና ኃላፊነት እንዲሁም የሃገሪቱን የመድኃኒት አቅርቦት ሁኔታ ግንዛቤ አስጨብጠዋቸዋል፡፡
አስተባባሪው የልዑካን ቡድኑ ኢትዮጵያ ውስጥ 3 ቀን ቆይታ እንዳለው ገልፀው በቆይታቸውም የተለያዩ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታሎችና የጤና ሴክተሮችን ጉብኝት አድርገዋል ሲሉ አብራርተዋል፡፡
ስዊዲን ከኤጀንሲው ጋር ግንኙነት ካላቸው የተለያዩ አጋር ድርጅቶች ጋር ግንኙነት እንዳላትና ከፍተኛ ድጋፍም ታደርጋለች ሲሉ አስተባባሪው አክለው ገልጸዋል፡፡