የተለያዩ የሚዲያ አካላት የሐዋሣን ቅርንጫፍ ጎበኙ፡፡
December 9, 2019ፊውቸርድ ዜና
የተለያዩ የመንግሥት እና የግል ሚዲያ አካላት ህዳር 26 ቀን 2012 ዓ.ም. የሐዋሣ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት፣ መጋዘን እና የመድኃኒት ማክሠሚያ/ኢንሲኔሬተር ጉብኝት አካሄዱ፡፡
የቅርንጫፉ ሥራ አስኪያጅ አቶ ዘመን ለገሠ ቅርንጫፉ ስለሚሠጣቸው አጠቃላይ አገልግሎቶች ለተሣታፊዎቹ ግንዛቤ ያስጨበጡ ሲሆን ለ505 የጤና ተቋማት ቅርንጫፉ አገልግሎት እንደሚሠጥ አስረድተዋል፡፡
የሐዋሣ ቅርንጫፍ 4500 ሜትር ኪዩብ የመድኃኒት ማከማቻ እንዳለው እና 3090 የመድኃኒት ማስቀመጫ ቦታ እንዳለው ገልፀው ቅርንጫፉ በ1 ጊዜ 4 መኪኖችን መጫን እንደሚችል ሥራ አስኪያጁ አብራርተዋል፡፡
የሚዲያ አካላቱ የሐዋሣ የመድኃኒት ማክሠሚያን /ኢንሲኒሬተር/ የጎበኙ ሲሆን በ5000 ካሬ ላይ ማረፉን፣ በሠዓት እስከ 5ዐዐ ኪ.ግ እንደሚያቃጥልና 1400 ዲግሪ ሴንቲ ግሬድ የማቃጠል ኃይል እንዳለው አስረድተዋል፡፡
በእለቱ የሕዝብ ግንኙነት እና ኮሙኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ወ/ሮ አድና በሬ በኤጀንሲው ድረ-ገፅ ለደንበኞች የሚሠጡ አገልግሎቶችን ገለፃ አድርገዋል፡፡ በጉብኝቱ ላይ 13 የመንግስት እና የግል ሚዲያዎች ተገኝተዋል፡፡