ለስኳር ህክምና አገልግሎት የሚውሉ በቂ መጠን ያለው መድኃኒት እየተሰራጨ መሆኑ ተገለፀ። =======================
ኤጀንሲው ለስኳር ህሙማን ህክምና አገልግሎት የሚውሉ መድኃኒቶችን ከየካቲት 2013 ዓ.ም ጀምሮ ካለው የፍጆታ መጠን አንፃር በቂ የሆነ መድሀኒት ማሰራጨት መጀመሩን የስርጭት ባለሞያ ወ/ሪት ምህረት ጌታሁን አስታወቁ።
መድሀኒቶቹም Insulin Soluble 100lU/ml እና Insulin Isophane Biphasic Mixture(30+70)lU/ml ናቸው።
ለስኳር በሽታ ደረጃ 1 እና 2 ህሙማን እንድሁም ከስኳር ህመም ጋር ተያይዘው ለሚከስቱ የጤና እክሎች የሚውሉ መድኃኒቶች መሆናቸውን ባለሞያዋ አብራርተዋል።የመድኃኒት ስርጭቱም በሁሉም ቅርንጫፎች አማካኝነት ለጤና ተቋማት እየተካሄደ ሲሆን 12 ሚሊዮን 72 ሺህ 679 ብር ወጪ እንደተደረገበት ተገልጿል።በአሁኑ ወቅት ለስኳር ታካሚዎች የሚሆን በቂ መድሀኒት ያለ አና እየተሠራጨ በመሆኑ ህብረተሰቡ አጥረት አለ ብሎ መጨናነቅ የለበትም።