የኢትዮጵያ መድኃኒት አቅራቢ አገልሎት ከባለድርሻ አካላቱ ጋር ከህዳር 28 – 29/2016 ዓ.ም. በአዳማ ከተማ ያካሄደው የምክክር አውደ ጥናት ተጠናቀቀ፡፡ በተደረገው ምክክር የመድኃኒት አቅርቦት ሰንሰለቱ የተቀላጠፈ እና ይበልጥ ውጤታማ እንዲሆን በሁሉም ባለድርሻ አካላት የተለዩ የአሰራር ማነቆዎች በጋራ ተለይተው እና ምክክር ተደርጎባቸው ችግሮቹ የሚፈቱበትን የድርጊት መርሃ- ግብር በማዘጋጀት ውይይቱ ተጠናቋል። የአገልግሎቱ ም/ዋና ዳይሬክተር አቶ አቅናው ካውዛ ከባለድርሻ […]