“ERP_SAP” ን ስራ ማዋል የተቀናጀ ዘመናዊ የጤና ስርአት (Digital Health) ለመፍጠር ያስችላል ተባለ
የኢትዮጵያ መድኃኒት አቅራቢ አገልግሎት በቅርብ ቀን ስራ ላይ የሚያውለው እጅግ ዘመናዊ የተቀናጀ “ERP_SAP” የተባለውን ፕሮጀክት አሁን ያለበት ደረጃ ምን እንደሚመስል የአገልግሎቱ ከፍተኛ አመራሮች ፣ ዳይሬክተሮች ፣ሰራተኞች እና የፕሮጀክቱ ሰራተኞች እንዲሁም የጤና ሚኒስቴር ሚንስትር ዴኤታ አማካሪ ወ/ሮ ሰሚራ ሱልጣን እና የዲጅታል ሄልዝ ባለሙያወች በተገኙበት ሰሞኑን በአዳማ ከተማ ኦሬንቴሽን ተሰጥቷል።
የመረጃ ስርዓቱ እንደ ሀገር የተያዘውን የጤና ስርአት (Digital Health) በመፍጠር ፤ የቁጥጥር ስራዎችን በማቅለል ጤናማ ኦዲት እንዲኖር በማስቻል ለሌሎች አገልግሎት ሰጪ ተቋማት አርአያ ይሆናል ሲሉ የአገልጎሎቱ ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር አብዱልቃድር ገልገሎ ተናግረዋል።
ጤና ሚኒስቴር ስራዎችን ዲጅታላይዝ ለማድረግ ሰፊ ተግባራትን እያከናወነ በመሆኑ ፕሮጀክቱን እንደ ባለቤት ሆነን በጋራ እንሰራለን ሲሉ ወ/ሮ ሰሚራ ሱልጣን የተናገሩ ሲሆን ፤ ሲስተሙ ሲተገበር ምንም አይነት እንቅፋት ሳያገጥመው አገልግሎት አሰጣጡን ምቹ ለማድረግ ሁሉም አካላት የዚህ የለውጥ ባለቤት በመሆን የራሱን ኃላፊነት በመወጣት ተፈፃሚ እንዲሆን መስራት እንደሚገባ ገልፀዋል።
የሲስተሙ ብዙ ስራወች በእቅዱ መሰረት መጠናቀቃቸውን እና በተለይም ጥራቱን የጠበቀ መረጃ ወደ ሲስተሙ ማስገባት ትልቅ ትኩረት ተሰጥቶ የተሰራበት ጉዳይ መሆኑን የፕሮጀክቱ የሶፍትዌር ዴቨሎፕመንት ባለሙያ አቶ እዩኤል አቤል አንስተው ፤ ፕሮጀክቱ ወደ ትግበራ ሲገባ ሊያጋጥሙ የሚችሉ ተግዳሮቶች ተለይተው የማስተካከል ስራ እየተሰራ ነው ብለዋል።
በተጨማሪ ለትግበራው የሚያስፈ
ልጉ የሰርቨር ፣ ዳታ ሴንተር ፣ኔትወርክ እና የደህንነት(security) መሰረተልማቶች እየተሟላ እንደሚገኝ እና የኔትወርክ ተደራሽነቱን የተሳለጠ ለማድረግ አገልግሎቱ ከኢትዮቴሌኮም ጋር በመተባበር የራሱን VPN ኔትወርክ እየዘረጋ እንደሚገኝ የፕሮጀክቱ የኔትወርክ እና ደህንነት ባለሙያ አቶ ይታመን አየለ ገልፀዋል።
አገልግሎቱ ሲጠቀምባቸው የቆየውን የቪታስ ፣ ፋኖስ ፣ ዳጉ2 እና ሌሎች ሶፍትዌሮች ከኢ.አር.ፒ ሲስተም ጋር አቀናጅቶ በመጠቀም የአቅርቦት ስርአቱ ሳይስተጓጎል በሂደት ሙሉ ለሙሉ ወደ ERP ሲስተም የማስገባት ስራ እንደሚከናወን ዋና ዳይሬክተሩ ተናግረው ፤ ደህንነቱ የተረጋገጠ ሲስተም እንዲሆን ለማስቻል ከኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር (INSA) እና ከአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩቱ ጋር ውል በመግባት ስራዎች እየተከናወኑ መሆኑን አክለው ገልፀዋል።
ማገልገል ክብር ነው
ሰላም ይደግ