HIV Viral Load ምርመራ የሚውሉ ግብዓቶች ወደ ኤጀንሲው መጋዘን መግባታቸው ታወቀ፡፡
![HIV Viral Load ምርመራ የሚውሉ ግብዓቶች ወደ ኤጀንሲው መጋዘን መግባታቸው ታወቀ፡፡](https://epss.gov.et/wp-content/uploads/2019/11/photo_2019-11-26_03-53-07-1024x760.jpg)
November 27, 2019ፊውቸርድ ዜና
በግዢ ሂደት ላይ የነበሩ ለHIV Viral Load ምርመራ የሚውሉ ከ50 በላይ የላብራቶሪ ሪኤጀንቶችና ግብዓቶች ወደ ኤጀንሲው መጋዘን መግባታቸውን የፕሮግራም ላብራቶሪ ግብዓቶች ትንበያና ገበያ ጥናት ባለሙያ አቶ ሳሙኤል ወንድወሰን ህዳር 16 ቀን 2012 ዓ.ም. ለዝግጅት ክፍሉ አስታወቁ፡፡
ሪኤጀንቶቹ እና ግብዓቶቹ በኤጀንሲው ቅርንጫፎች አማካኝነት ለተመረጡ 19 የHIV Viral Load ምርመራ ማእከሎች እንደሚሰራጩና ለአገልግሎት ዝግጁ እንደሚደረጉ ባለሙያው አብራርተዋል፡፡
ኤጀንሲው ያስገባቸውን ሪኤጀንቶችና ግብዓቶች ከጤና ተቋማት ፍላጎትና ሪፖርት በመነሳት ማን ምን ያህል ተጠቀመ? ምን ያህል ይፈልጋል? የሚለውን በማጥናት የላብራቶሪ ሪኤጀንቶች ምጣኔና ትንበያ እንደሚካሄድ አቶ ሳሙኤል አክለው ተናግረዋል፡፡
ራሔል ታመነ