TD የተሠኘው አዲስ የክትባት መድኃኒት ወደ ኤጀንሲው መግባቱ ተገለፀ፡፡
February 5, 2020ፊውቸርድ ዜና
እናቶች በእርግዝና ወቅት የሚሠጣቸው ቲታነስ ቶክሶይድ /TT/ እየተባለ የሚጠራው የክትባት መድኃኒት ተሻሽሎ ቲታነስ ቶክሶይድ + ዲፍቴሪያ /TD/ የክትባት መድኃኒት ወደ ኤጀንሲው መግባቱ ተገለፀ፡፡
የተሻሻለው መድኃኒት ለሁለት በሽታ መከላከያነት እንደሚውልና /TT/ Clostridium Tetanus በሚል ባክቴሪያ የሚመጣውን በሽታ ለመከላከል የሚሠጥ የክትባት መድኃኒት ሲሆን ተጨማሪው ክትባትም Diphteria በሚባል ባክቴሪያ የሚያመጣውን የትክትክ በሽታን ይከላከላል፡፡
የተሻሻለው የክትባት መድኃኒትም በ1 ድንጋይ ሁለት ወፍ እንደምንለው በ1 ክትባት ሁለት አይነት በሽታዎችን መከላከል የሚያስችል ሲሆን ከግዜም፣ ከገንዘብም አንፃር በርካታ ጠቀሜታዎች አሉት፡፡