የኢትዮጵያ መድኃኒት አቅራቢ ኤጀንሲ ለቲቢ ምርመራ አገልግሎት የሚውል መመርመሪያ ኪት ከሀምሌ እስከ መስከረም ባሉት ወራት በተከታታይ እያሰራጨ መሆኑን ከመጋዘን አያያዝና አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡የተሰራጨው መመርመሪያ ኪት ( Urine TB-LAM) የተሰኘ ሲሆን የበሽታ መከላከል አቅማቸው (CD4) ከ200 በታች የሆኑ የኤች አይቪ ህሙማን የቲቢ በሽታ በውስጣቸው መኖር፣ አለመኖሩን በቀላሉ በሽንት ለማረጋገጥ የሚረዳ መመርመሪያ መሆኑንን ለመረዳት ተችሏል፡፡ […]