በኢትዮጵያ የመድኃኒት አቅራቢ ኤጀንሲ የሐዋሳ ቅርንጫፍ ባለፉት 2 ዓመታት በከይዘን ትግበራ ባስመዘገበዉ ዉጤት ሞዴል ተቋም ሆኖ ተሞክሮዉን አቀረበ።የኢትዮጵያ የከይዘን ኢንስቲትዩት የከይዘን ፍልስፍና ትግበራን በመላ ሐገሪቱ ለማስረጽ የተለያዩ እስትራቴጂዎችን በመንደፍ ተግባራዊ እያረገ ይገኛል፡፡ከነዚህም አንዱ በከይዘን ትግበራ ሞዴል የሆኑ ተቋማትን በማፍራትና የትግባራ ተሞክሯቸዉን በማስፋት በሐገሪቱ ምርታማነትን ማሳደግ ነዉ፡፡ በዚሁ መሠረት በከይዘን ዙሪያ የተሰሩ ጥናታዊ ጽሑፎችና የተቋማት ተሞክሮ […]