ኤጀንሲው ለ2014 በጀት ዓመት የህክምና ግብዓቶችና የመድኋኒት ፍላጎት ምጠና እያካሄደ መሆኑን የግዥ ትንበያና ገበያ ጥናት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ሀብቱ በርሔ ታህሳስ 10 ቀን 2012 ዓ.ም አስታወቁ፡፡የመድኋኒት ምጠናው ለጤና አገልግሎት የሚያስፈልጉትን የሕክምና መገልገያና መድኋኒት ብዛትና ወጪውን የመገመት ሂደት መሆኑንና የተመቻቸና የማያቋርጥ አቅርቦትን ለማረጋገጥ ትዕዛዞች መቼ መሰጠት እንዳለባቸው መወሰን ነው ሲሉ ዳይሬክተሩ ተናግረዋል፡፡አክለውም የመድኋኒት ምጠና የቁጥር ማረጋገጫ፣ […]