የኢትዮጵያ መድሀኒት አቅራቢ ኤጀንሲ በቀጣይ ሁለት አመታት ለሚያቀርባቸው የመድሀኒት ግዥ መዘርዝ /pharmaceuticals procurement list /ከባለድርሻ አካላት ጋር አውደ ጥናት ከነሀሴ 25-27/2012 ዓ.ም ድረስ በአዲስ አበባ ተካሂዷል። የመድኃኒት ግዥ መዘርዝሩ በየሁለት አመቱ የሚከለስ እንደሆነ እና በሂደት ላይ ያለውን መዘርዝር በጥልቀት በማየት፣ ከመዘርዝሩ ውስጥ የሚካተቱ፣ የሚወጡ፣በብዛት ተላላፊ ለሆኑ እና ላልሆኑ በሽታዎች የሚሆኑ፣አዋጭ ዋጋ ያላቸውን እና የጋራ መለያ […]