(Tenofovir+Lamivudine+Efavirenz) የተባለው የጸረ ኤች አይቪ መድኃኒት የ Efavirenz ጥንካሬ (strength) ከ600mg ወደ 400mg መቀነሱ ተገለጸ፡፡ =======================================
በኢትዮጵያ መድኃኒት አቅራቢ ኤጀንሲ የአለም ጤና ድርጅትን የጥናት ምክረ ሃሳብ መሰረት ተደርጎ የጸረ ኤች አይቪ መድኃኒቱ ግራም መቀነሱን እና መድኃኒቱን ማቅረብ መጀመሩን በኤጀንሲው የኤች ኤ ቪ ፡ተቢ እና ወባ ምጠና ቡድን መሪ ወ/ሪት ፂወን ፀጋየ የካቲት 5/2012 ዓ.ም ገልጸዋል፡፡
የጸረ ኤች አይቪ መድኃኒቱ ከአሁን በፊት Tenofouir300mg+Lamivudine300mg+Efavirenz 600mg እንደነበረ ገልጸው በአሁኑ ወቅት Tenofouir300mg+Lamivudine300mg+Efavirenz 400mg እንድቀየር ተደርጓል በማለት ተናግረዋል፡፡
የ Efavirenz መጠኑ ከ 600 mg ወደ 400 mg ዝቅ ያለበት ምክንያት የመድኃኒቱን የጎንዮሽ ጉዳት ለመቀነስ ሲባል መሆኑን ገልጸው ለነብሰጡር እና የቲቢ መድሃኒት እየወሰዱ ላሉ ታካሚዎችም ከሌሎች መድኃኒቶች ጋር አብሮ መወሰድ የሚችል መሆኑን አብራርተዋል፡፡
በጤና ሚንስቴር የኤች ኤይ ቪ ህክምና መመሪያ /HIV Treatment guideline/ላይ Efavirenz ባለ 400 በዝርዝሩ መካተቱን ገልጸው የአለም ጤና ድርጅትን /WHO/ ምክረ ሃሳብ እና የሚኒስቴር መስሪያቤቱን አቅጣጫ በመከተል በግሎባል ፈንድ በጀት መድኃኒቱ እየተሰራጨ እንዳለ እና የኤች እይ ቪ ምርመራ ለሚሰጡ ጤና ተቋማትም ግንዛቤ እንዲኖራቸው መደረጉን ቡድን መሪዋ አክለው ገልጸዋል፡፡
Supply chain of compassion!!!!!!!!