ጠቅላይ ሚኒስትሩ ዛሬ በፅህፈት ቤታቸው በሰጡት መግለጫ በዩኒቨርሲቲዎች ተማሪዎች ባሉበት ሆነው አስፈላጊው ክትትል ይደረግላቸዋል ብለዋል። አስፈላጊ ከሆነም አነስተኛ ስብሰባዎች በጤና ሚኒስቴር እውቅና እና ክትትል ሊደገፉ እንደሚገባም ገልጸዋል። ግብዓትን በተመለከተ ሳሙና አልኮልን ጨምሮ ሌሎች የንፅህና መጠበቂያዎች በስፋት እንደሚሰራጩም አስታውቀዋል። እነዚህን የንፅህና መጠበቂያዎች ሰዎች በቀላሉ እንዲያገኟቸው በተለያዩ አካባቢዎች እንዲቀመጡ ይደረጋልም ነው ያሉት። በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች አሁን ላይ […]