Medical Articles & News
የኢትዮጵያ መድኃኒት አቅራቢ አገልግሎት በመድሃኒት የግዥ መዘርዝሩ ተካተው በመላ ሀገራችን ለሚገኙ ጤና ተቋማት የግብአቶችን ምጠና በማድረግ በግዥ ከሚያቀርባቸው፣ ከሚያከማቻቸው እና ከሚያሰራጫቸው የተመረጡ ከአስራ ሁለት (12) አይነት በላይ ለሰመመን ህክምና ከሚውሉት ግብአቶች ውስጥ ከሰክሳሚቶኒየም (Suxamethonium) በስተቀር በሌሎቹ ላይ እጥረት እንደሌለ የአገልግሎቱ ም/ዋና ዳይሬክተር አቶ ሰለሞን ንጉሴ ግንቦት 7 ቀን 2014 ዓ.ም ገለፁ።በመሆኑም መድሀኒቱን ከሚመረትበት ሀገር በዘላቂነት […]
የኢትዮጵያ መድኃኒት አቅራቢ አገልግሎት በአማራና አፋር ክልሎች በጦርነቱ የወደሙ ጤና ተቋማትን መልሶ ለማቋቋምና የተሟላ አገልግሎት እንዲሰጡ ለማስቻል ከጤና ሚንስቴር በድጋፍ የተገኙ ከ70 አይነት በላይ የህክምና መሳሪያዎችን ከመጋቢት 22 ቀን 2014 ዓ.ም ጀምሮ ማሰራጨቱን የባዮ ሜድካል ኢንጅነር የሆኑት አቶ የቻለ ሽፈራው ገለጹ፡፡ከተሰራጩት የህክምና መሳሪያዎች መካከል ICU-bed, Oxygen concentrator, ECG Machine, Sterilizer, Monitor-Patient, Mechanical Ventilator, Couch-Delivery, Microscope-Binocular, […]
የኢትዮጵያ መድኃኒት አቅራቢ አገልግሎት ጠንካራ የመረጃ ስርዓት እንዲኖር የ ERP ፕሮጀክትን በተለያዩ ምዕራፎች እንዲተገበር እየሰራ ሲሆን ከአሁን በፊት በተቆራረጠ መልኩ ሲተገበር የነበረውን የመረጃ ፍሰት ወደ ተቀናጀ እና እርስ በርስ የሚናበብ የመረጃ ስርዓት በመሆኑ ለመድኃት አቅርቦት ሠንሠለቱ ከፍተኛ ጠቀሜታ እንዳሚኖረው የአገልግሎቱ የፋይናንስ እና የጤና ስርዓት ማጠናከር ዘርፍ ም/ዋና ዳይሬክተር አቶ አቅናው ካውዛ ገለፁ፡፡ም/ዋ ዳይሬክተሩ በ change […]
የኢትዮጵያ መድኃኒት አቅራቢ አገልግሎት በጤና ተቋማት ተኝተው ለሚታከሙ ህሙማን በሰውነታቸው ውስጥ ያሉትን ንጥረ ነገሮች ለመተካት የሚረዳ Normal Saline/NS/ የተባለ ነብስ አድን ወደ ሀገር ውስጥ ገብቶ ለጤና ተቋማት እየተሰራጨ መሆኑን የአገልግሎቱ ም/ዋና ዳይሬክተር አቶ ሰለሞን ንጉሴ ሚያዝያ 6 ቀን 2014 ዓ.ም ገለጸ፡፡ ከህንድ ሀገር እየገባ እና እየተሰራጨ ያለው ብዛቱ 80 ኮንቴነር በላይ የሆነ 1 .8 ሚሊዮን […]
የኢትዮጵያ መድኃኒት አቅራቢ አገልግሎት የክትባት መድኃኒቶችንም ሆነ ሌሎች የህክምና ግብዓቶችን ገዝቶ በማስገባት፣ በማከማቸትም ሆነ በስርጭት ሂደት የባለደርሻ አካላት ቅንጅት ለስራው ቁልፍ መሆኑ ከአዳማ ከተማ በተደረገ የምክክር ወርክሾፕ ተገልጿል፡፡የክትባት መድኃኒቶችን በግዥ እንዲያቀብለን ለዩኒሴፍ ውክልና ተሰጥቶ የኢትዮጵያ መድኃኒት አቅራቢ አገልግሎት በመረከብ የማከማቸትና የማሰራጨት ስራ ይሰራል ያሉት ለጤና ሚኒስቴር የእናቶች ፣ ህፃናት ዳይሬክቶሬት ረዳት ዳይሬክተር እና የብሄራዊ ክትባት […]
የኢትዮጵያ መድኃኒት አቅራቢ አገልግሎት በፕሌስመንት ግዥ ያስገባቸውን 58 አይነት ሪኤጀንቶች ከመጋቢት 12 እስከ 23 ቀን 2014 ዓ.ም ማሰራጨቱን የመድኃኒትና ክምችት ባለሙያ አቶ ብሩክ ክፍሌ ገለጹ፡፡ የተሰራጩት የdimension DXL200 ሪኤጀንቶች ሲሆኑ ለጉበት ፣ለኩላሊት፣ለኮልስትሮልና ለኤሌክትሮ ላይት ምርመራ አገልግሎት እንደሚውሉ አቶ ብሩክ ተናግረዋል፡፡ስርጭቱም በደሴ፣ በባህርዳር፣ በአርባ ምንጭ፣ በጅማ፣ በሰመራና በሀዋሳ ቅርንጫፎች አማካኝነት ለደቡብ ብሔር ብሔረሰቦችና ህዝቦች፣ ለአማራ፣ ለኦሮሚያና […]
አገራዊ ጥሪውን ተከትሎ ዳያስፖራው በጦርነቱ ለተጎዱ የጤና ተቋማት 110 ሚሊዮን ብር የሚገመት የመድኃኒትና የህክምና ቁሳቁስ ድጋፍ ማድረጉን የኢትዮጵያ መድኃኒት አቅርቦት ኤጀንሲ አስታወቀ።መንግስት በጦርነቱ የተጎዱ ተቋማቱን መልሶ በማቋቋም ሂደት በውጭ የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን ድጋፍ እንዲያደርጉ ጥሪ ማድረጉ ይታወቃል።ይህንን ተከትሎም በተለያዩ አገራት የሚኖሩ የዳያስፖራ ማህበረሰብ አባላት በጦርነቱ የተጎዱ አካባቢዎችን መልሶ ለማቋቋም የተለያዩ ድጋፎችን እያደረጉ ሲሆን፤ በተለይ የህክምና ተቋማትን […]
የኢትዮጵያ መድኃኒት አቅርቦት አገልግሎት 400 ሚሊዮን ብር ወጪ የተደረገባቸውን ዘመናዊ የሕክምና መሳሪያዎች ለጤና ተቋማት ተደራሽ ማድረጉን አስታወቀ፡፡እነዚህ መሳሪያዎች በተለያየ ምክንያት ሳይገዙ የቆዩ የህክምና መሳሪያዎች መሆናቸውም ታውቋል።አገልግሎቱ የሕክምና መሳሪያ እጥረት ችግር ለመቅረፍ የሚያስችል ስራዎች እየሰራ እንደሆነም ገልጿል።የአገልግሎቱ ዋና ዳይሬክተር ዶክተር አብዱልቃድር ጋልጋሎ ለኢዜአ እንደገለጹት፤ ውል ተገብቶባቸው ሳይገዙ የቆዩ የህክምና መሳሪያዎችን በ400 ሚሊዮን ብር ወጪ ተገዝተው ወደ […]
የኢትዮጵያ መድኃኒት አቅራቢ አገልገግሎት ለጤና ተቋማት የሚያቀርባቸውን መደበኛም ሆነ የኮሮና ክትባቶች የተቀመጠላቸውን የሙቀት እና ቅዝቃዜ ስታንዳርድ ተጠብቆላቸው ወደ ሀገር ውስጥ ሲገቡ ፈዋሽነታቸውን ጠብቀው መሆን እንዳለት ለዚህም የቁልፍ ባለድርሻ አካላት ሚና ከፍተኛ መሆኑን አቶ ሰለሞን ንጉሴ የአገልግሎቱ ም/ ዋና ዳይሬክተር መጋቢት 17 ቀን 2014 ዓ.ም ተናግረዋል፡፡ከቁልፍ ባለ ድርሻ አካላት ጋር የተደረገው ምክክር በዋነኛነት በክትባቶች አስተዳደር ሂደት […]