የኢትዮጵያ መድኃኒት አቅራቢ አገልግሎት ለማህፀን በር ካንሰር ህክምና አገልግሎት የሚውል የህክምና መሳሪያ ማሰራጨቱን የመድኃኒት ክምችትና ስርጭት ባለሙያ አቶ የቻለ ሽፈራው ጥር 9 ቀን 2014 ዓ.ም አስታወቁ፡፡ የተሰራጨው የህክምና መሳሪያ Cryotherapy unit-Cervical ሲሆን 24 ሚሊየን 969 ሺህ 138 ብር ወጪ ተደርጎበታል፡፡ ስርጭቱም በኤጀንሲው ቅርንጫፎች አማካኝነት ለደቡብ ብሄር ብሄረሰቦችና ህዝቦች ክልል፣ ለጅጅጋ፣ ለሲዳማ፣ ለአማራ፣ ለኦሮሚያ፣ ለሶማሌ፣ለአፋር፣ለድሬደዋና ለአዲስ […]