በኢትዮጵያ የማርበርግ ቫይረስ በሽታን ሙሉ በሙሉ መቆጣጠር መቻሏን ይፋ ተደርጓል።
News
January 26, 2026
128 views

በኢትዮጵያ የማርበርግ ቫይረስ በሽታን ሙሉ በሙሉ መቆጣጠር መቻሏን ይፋ ተደርጓል።

በኢትዮጵያ የማርበርግ ቫይረስ በሽታን ሙሉ በሙሉ መቆጣጠር መቻሏን ይፋ ተደርጓል።

በዓለም ጤና ድርጅት (WHO) እንዲሁም በሃገራችን የማርበርግ በሽታ ቅኝት እና ምላሽ መመሪያ መሰረት ወረርሽኙ ሙሉ በሙሉ በቁጥጥር ስር መዋሉ የሚታወጀው የመጨረሻዉ የማርበርግ ታማሚ ከነበረበት 42 ቀናት ዉስጥ ሌላ ተጨማሪ በበሽታው የተያዘ እንዲሁም ህይወቱ ያለፈ ሰው አለመኖሩ ሲረጋገጥ መሆኑ ይታወቃል።

በኢትዮጵያ የማርበርግ ቫይረስ በሽታ ወረርሽኝ መከሰቱን ከታወጀበት እና የመጀመሪያው የወረርሽኙ ታማሚ መገኘቱን ከታወጀበት ህዳር 5/2018 ዓም ጀምሮ በወረርሽኙ የተጠረጠሩ ዜጎችን የመርመር እና የተገኘባቸውን ዜጎችን የመለየት ስራዎች ሲሰሩ ቆይተዋል።

በአጠቃላይ ከ 3 ሺ 800 በላይ ምርመራዎች የተከናወኑ ሲሆን ወረርሽኙ የተገኘባቸው ዜጎች ቁጥርም 14 ነበር።

በበሽታው ከተያዙ ዜጎች ውስጥ የዘጠኙ ህይወት ያለፈ ሲሆን 5 ቱ አገግመው ከቤተሰቦቻቸው ጋር መቀላቀል ችለዋል።

የኢትዮጵያ ድንገተኛ የማሕበረሰብ ጤና አደጋ ፈጣን ምላሽና አመራር ስኬቶች እንዲሁም የማርበርግ ቫይረስ በሽታ ቁጥጥር ማብሰሪያ መድረክ በዛሬው ዕለት የተካሄደ ሲሆን በመድረኩም ባለፉት 42 ቀናት ምንም አይነት የወረርሽኙ ተጠቂ አለመገኘቱ ተገልጿል።

በእዚህም መሰረት በዓለም ጤና ድርጅት (WHO) እንዲሁም በሃገራችን የማርበርግ በሽታ ቅኝት እና ምላሽ መመሪያ ፕሮቶኮል መሰረት ወረርሽኙ ሙሉ በሙሉ በቁጥጥር ስር መዋሉ ተበስሯል።

ኢትዮጵያ ከወረርሽኙ ነጻ መሆኗን የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባዔ ታገሰ ጫፎን መድረኩ ላይ አብስረዋል።

በመድረኩ የክልል ርዕሰ መስተዳድሮች፣ የጤና ሚኒስትር ከፍተኛ ሃላፊዎች ጨምሮ በርካታ ባለድርሻ አካላት ተገኝተዋል።

በመድረኩ ንግግር ያደረጉት የጤና ሚኒስትር ሚኒስቴር ዶ/ር መቅደስ ዳባ "የዘጠኝ ሰዎች ህይወት በወረርሽኙ ህይወታቸው ቢያልፍም ወረርሽኙ ያደርስ ከነበረው ውስብስብ ችግር አንጻር ሃገራችንንን መታደግ ችለናል" ብለዋል።

በተጨማሪም"የመጨረሻው ታካሚ በላብራቶሪ ህክምናው ነጻ ሆኖ ከተረጋገጠበት 42 ተከታታይ ቀናት ምንም አይነት አዲስ ታካሚ ባለመመዝገቡ ወረርሽኙ በቁጥጥር ስር መዋሉን በይፋ በምንናገርበት በዛሬው ቀን ላይ ደርሰናል"ሲሉ አክለዋል።
Share this article:
🤖
EPSS Assistant Online · Ethiopian Pharmaceuticals Supply Service