የመድኃኒት አቅርቦት ሰንሰለትን ለማዘመን እና ለአስተማማኝ የመድኃኒት የመገኘት ምጣኔ ገንቢ አስተዋፅኦ ያለው የጥናት ውጤት ለውይይት ቀረበ ፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨
News
March 03, 2026
37 views

የመድኃኒት አቅርቦት ሰንሰለትን ለማዘመን እና ለአስተማማኝ የመድኃኒት የመገኘት ምጣኔ ገንቢ አስተዋፅኦ ያለው የጥናት ውጤት ለውይይት ቀረበ ፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨

ሚኒስትር ዴኤታዋ ወ/ሮ ፍሬሂወት አበበ ባስተላለፉት መልእክት፣ በጥናቱ የተለዩ ግኝቶች በሚቀጥሉት 3 ዓመታት እቅድ ውስጥ ተካተው ተግባራዊ እንደሚሆኑ ገልጸው፣ የመረጃ ግልጽነትን በማረጋገጥ እና የአቅርቦት ሰንሰለቱን በማዘመን በኩል የተጀመሩ ስራዎች ተጠናክረው መቀጠል እንዳለባቸው አጽንኦት ሰጥተዋል።

እንዲሁም የመድኃኒት የዋጋ መረጋጋትንና የግብዓት እጥረትን ለመቅረፍ የሚያስችሉ ተግባራዊ እርምጃዎች ከውይይቱ እንደሚጠበቁ ተጠቁሟል።

የአገልግሎቱ ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር አብዱልቃድር ገልገሎ በበኩላቸው፣ አገልግሎቱ የተረጋጋ የገበያ ስርዓት በመፍጠር ያልተቆራረጠ አቅርቦት ለማረጋገጥ እየሰራ መሆኑን አስታውሰዋል።

በጥናቱ አቅራቢዎችም በዋጋ አወጣጥ፣ በአቅርቦት መረጋጋት፣ በጥራት እና በፍላጎት ትንበያ ስርዓት ላይ ያሉ ክፍተቶችና እድሎች ተብራርተዋል።

የጥናቶቹን ውጤቶች በውይይት ከዳበሩ በሗላ የመድኃት አቅርቦት ሰንሠለቱን አስተማማኝ ለማድረግ ግኝቶቹን እንጠቀምባቸዋለን ብለዋል።

በጥናቱ በመድኃኒት አቅርቦት ሠንሠለቱ ከላይ እስከ ታች ያሉ ክፍተቶች የተለዩ ሲሆን እነዚህን እጥረቶች ለመሙላት የሚረዱ ሳይንሳዊ መፍትሄዎችን አካቷል።

ተሳታፊዎች በጥናቱ ላይ ሰፊ ውይይት ያደረጉ ሲሆን፣ በጋራ በተደረገው የቴክኒክና የአቅም ግንባታ ድጋፍ Result for Development (R4D) ኢትዮጵያ አስተዋፅኦ ማድረጉ ተገልጿል።

#ማገልገል ክብር ነው!
Share this article:
🤖
EPSS Assistant Online · Ethiopian Pharmaceuticals Supply Service