የኢትዮጵያ መድኃኒት አቅራቢ አገልግሎት የሀገር ውስጥ መድኃኒት አምራቾችን ለማበረታት አዲሱን የግዥ መመሪያ መሰረት በማድረግ እስከ 7ዓመት የሚቆይ ውል በመፈፀም ዋስትና ያለው ገበያ እየፈጠረ ድጋፍ እያደረገ ይገኛል።
በዚህም የሀገር ውስጥ ምርት በተያዘው በጀት ዓመት 42% ማድረስ እንደተቻለ የአገልግሎቱ ም/ዋና ዳይሬክተር አቶ አቅናው ካውዛ ተናግረዋል።
ይሁን እንጂ አምራቾች ውል አፈፃፀማቸው የተወሰነ ክፍተት መኖሩን አንስተው ለአቅርቦት ሰንሰለቱ መሳለጥ ጊዜውን የጠበቀ አቅርቦት ወሳኝ መሆኑን ጠቁመዋል።
አክለውም አምራቾች ውል በገቡት መሰረት ለአገልግሎቱ የህክምና ግብአቶችን በማቅረብ አጋርነታቸውን አጠናክረው ሊቀጥሉ ይገባል ሲሉ አቶ አቅናው መልዕክት አስተላልፈዋል።
#ማገልገል ክብር ነው!
ሰላም ይደግ