የተቀናጀ የአቅርቦት ዕቅድ ክለሳ መስራት አቅርቦትን ከፍላጎት ጋር ለማጣጣም ትልቅ ሚና አለዉ
News
March 01, 2026
58 views

የተቀናጀ የአቅርቦት ዕቅድ ክለሳ መስራት አቅርቦትን ከፍላጎት ጋር ለማጣጣም ትልቅ ሚና አለዉ

የአትዮጵያ መድኃኒት አቅራቢ አገልግሎት ከተለያዩ ባለድርሻ አካላት ጋር ሲያከናዉን የቆየዉን የ2018 ዓ.ም የ2ተኛ ሩብ አመት የጤና ፕሮግራም ፣ የተገላባጭ ፈንድ እና የክትባት ግብአቶችን የአቅርቦት እቅድ ክለሳ አዉደ ጥናት አጠናቋል፡፡

በአዉደ ጥናቱ ባለፉት 3 ወራት አቅርቦት ከፍላጎት ጋር የተጣጣመ ስለመሆኑ ፤ የህክምና ግብአቶች ቀደም ሲል በተተነበየላቸዉ ፍጆታ መጠን መሰረት ጥቅም ላይ መዋላቸዉን በመገምገም የክምችት ስጋት ላይ የሚገኙ መድኃኒቶች ተለይተዉ የመፍትሄ አቅጣጫ ተቀምጧል፡፡

አቅርቦትን ከፍላጎት ጋር ለማመጣጠን በየሩብ አመቱ የእቅድ ክለሳ ማከናወን ትልቅ ሚና ይጫዎታል ሲሉ የአገልግሎቱ የመድኃኒትና የህክምና መገልገያዎች ፍላጎት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ወርቅነህ አበበ ተናግረዉ ፤ ብክነት እና የአቅርቦት መቆራረጥ እንዳይከሰት አስተዋጽኦ አለዉ ብለዋል፡፡

በቀጣይ ይህን የተቀናጀ የአቅርቦት ዕቅድ ክለሳ ለማጠናከር የሚያስችል ደረጃዉን የጠበቀ የዲጅታል ስርአት ለመዘርጋት ዘርፈ ብዙ ስራ እየተከናወነ መሆኑን አቶ ወርቅነህ ጠቁመዋል፡፡

#ማገልገል ክብር ነዉ!
ሰላም ይደግ
Share this article:
🤖
EPSS Assistant Online · Ethiopian Pharmaceuticals Supply Service