የኢትዮጵያ መድኃኒት አቅራቢ አገልግሎት (EPSS) ውል የተገባለትን የአቅርቦት ስርዓት (Commited Demind & Supply System - CDSS) አፈፃፀም በቅርበት ለመከታተል የሚያስችል አዲስ በውስጥ አቅም የተሠራ የዲጂታል ስርዓት በይፋ ወደ ስራ ማስገባቱን አስታወቀ።
አገልግሎቱ ይህንን ይፋ ያደረገው ከቅርንጫፍ ስራ አስኪያጆች እና ከዋናው መሥሪያ ቤት ዳይሬክተሮች ጋር የሩብ ዓመት የሥራ አፈፃፀም ግምገማ ባካሄደበት ወቅት ነው።
የስርዓቱ ፋይዳና ዝርዝር ይዘት
የኢንፎርሜሽን ኮሙኒኬሽን ቴክኖሎጂ ዳይሬክቶሬት የሲስተም ማበልፀግ ቡድን መሪ የሆኑት አቶ ሳሙኤል ጌታዬ እንዳብራሩት፤ አዲሱ የክትትል ስርዓት የሚከተሉትን ቁልፍ መረጃዎች በዝርዝር ያሳያል ብለዋል ።በዚህም
✅ ሳምንታዊ እና ወርሃዊ የመድኃኒት ሽያጮች በቀላሉ ይታወቃሉ፤
✅ የግብዓቶች መገኘት ምጣኔ በየደረጃው ይለካል፤
✅ ውል የተገባላቸው መድኃኒቶች በትክክል ለጤና ተቋማት መድረሳቸው ይረጋግጣል፤የክልል፣የዞን እና የወረዳ የህክምና ግብአቶች ፈሰትን ዳታዎችን መከታተል ያስችላል።
✅ ያልተሰበሰቡ ሂሳቦች (Receivables) ያለበት ደረጃ ያሳያል
✅በመጋዘን የህክምና ግብአቶች ክምችት በግልጽ ይታያሉ።
✅በውስጥ አቅም የበለፀገ በመሆኑ ለሌሎች ተጨማሪ የፈጠራ ስራዎች እድል ይፈጥራል።
✅ከዋና መጋዘን እስከ ክልሎች ያለውን አጠቃላይ የህክምና ግብአቶች የስርጭት ሂደት በቀላሉ መከታታል ያስችላል ።
✅ውል የገቡ የጤና ተቋማት ብዛት እና ትክክለኛውን የውል ስምምነት ተከትለው የቀረቡ ግብዓቶች በዝርዝር ያሳያል ።
✅ሌሎችም ፊውቸሮች በእየጊዜው እየተጨመሩበት ስራን ለማቃለል ፣ ለማቀላጠፍ እና ውሳኔ ለመወሰን ይጠቅማል።
የአገልግሎቱ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ሰለሞን ንጉሴ በበኩላቸው፤ ስርዓቱን ውጤታማ ለማድረግ በ EPSS፣ በጤና ሚኒስቴር እና በክልል ጤና ቢሮዎች መካከል ጠንካራ ቅንጅት መፈጠሩን ገልፀዋል።
በተጨማሪም በአገልግሎቱ ኮማንድ ሴንተር በኩል ማነቆ ሆነው የነበሩ መፍትሄዎችን የማበጀት፣ የሰራተኞችን ግንዛቤ የማሳደግ እና የክትትል ስራዎችን በትኩረት እንደሚከናወኑ አመልክተዋል።
የፍላጎት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ወርቅነህ አበበ በበኩላቸው፤ ለስርዓቱ ትግበራ የሚያስፈልጉ መመሪያዎች መዘጋጀታቸውንና የአፈፃፀም መለኪያ (KPI) ማዕቀፍ መቀረጹን ገልፀዋል።
ይህም በትግበራ ወቅት ሊያጋጥሙ የሚችሉ ስጋቶችን ለመቀነስና የ2019 የCDSS ዝግጁነትን ለማረጋገጥ ትልቅ እገዛ እንደሚያደርግ አስረድተዋል።
በመድረኩ ማጠቃለያ ላይ ይህንን የክትትል ስርዓት በማበልፀግ ረገድ ከፍተኛ ትጋት ላሳዩ የኢንፎርሜሽን ኮሙኒኬሽን ሙያተኞች እውቅና ተሰጥቷል ።
"ማገልገል ክብር ነው!"
ማህሌት አበራ