በዚሁ መሠረት በሰሜኑ ጦርነት ወቅት በሥራ ገበታቸው ላይ እያሉ ሕይወታቸውን ላጡት የደሴ ቅርንጫፍ የጥበቃ ሠራተኛ አቶ ቻለው ሸዋንግዛው፣ ተቋሙ የመኖሪያ ቤት ግንባታ በማከናወን ለቤተሰቦቻቸው አስረክቧል።
የተደረጉ ዋና ዋና ድጋፎች፦
#የመኖሪያ ቤት ስጦታ፦ የሟች ቤተሰቦች ከኪራይ ቤት ወጥተው የራሳቸው ቋሚ መጠለያ እንዲኖራቸው ተደርጓል ።
#የሥራ ዕድል ፈጠራ፦ የሟች ቤተሰቦች እንደ የትምህርት ደረጃቸውና እንደ ሙያቸው በተቋሙ ውስጥ የሥራ ዕድል እንደሚመቻችላቸው ቃል ተገብቷል ።
#ቀጣይነት ያለው ክትትል፦ ተቋሙ ለቤተሰቡ አስፈላጊውን ድጋፍ ማድረጉን እንደሚቀጥል ተረጋግጧል።
አቶ ታሪኩ በላቸው አክለውም፣ ተቋሙ ለሠራተኞቹ የሚያደርገውን መሰል ድጋፎች አጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልጸዋል።
በመኖሪያ ቤት ርክክብ ሥነ-ሥርዓቱ ላይ የወረዳውና የከተማ አስተዳደሩ የሥራ ኃላፊዎች፣ የተቋሙ ዳይሬክተሮችና ሠራተኞች በተገኙበት ቤቱ ለወይዘሮ መሬማ ሀሰን ተረክቧል።
#ማገልገል ክብር ነው!