የተሻለ የህክምና ግብዓት አቅርቦት ለመፍጠር ፍጥነት፣ ፈጠራና ማጥራት ያስፈልጋል
News
February 02, 2026
174 views

የተሻለ የህክምና ግብዓት አቅርቦት ለመፍጠር ፍጥነት፣ ፈጠራና ማጥራት ያስፈልጋል

የኢትዮጵያ መድኃኒት አቅራቢ አገልግሎት (EPSS) የ6 ወር እቅድ ክንውንን ከጥር 21–23 ቀን 2018 ዓ.ም ድረስ በዋና መስሪያ ቤቱ በሁሉም ዳይሬክቶሬቶች ተሳትፎ ገምግሟል።

በግምገማው ዘመናዊ አሰራሮችን በመተግበር፣ የመድኃኒት መገኘት ጥያቄን ለመመለስ የተጀመሩ ጅምር ስራዎች በፍጥነት፣ በፈጠራ እና በጥራት መከናወን እንዳለባቸው ተገልጿል።

ለሶስት ቀናት የተካሄደው ግምገማ ሂደት፣ የእያንዳንዱ ዳይሬክቶሬት አፈፃፀም በየዘርፉ በመገምገም የቅንጅታዊ አሰራር አስፈላጊነትን አሳይቶ ለተቋማዊ ራዕይ መሳካት በጋራ መትጋት እንደሚገባ ላይ ግንዛቤ አፍርሷል።

አገልግሎቱ ከ5,000 በላይ የጤና ተቋማት ጋር የ24 ቢሊየን ብር የህክምና ግብዓት አቅርቦት ውል የገባ ሲሆን፣ የቀጥታ የመድኃኒት ስርጭት አቅሙንም አሳድጎታል።

የተቋሙ ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር አብዱልቃድር ገልገሎ፣ አቅርቦትና ፍላጎትን ለማጣጣም እንዲሁም የገበያ ዋጋን ለማረጋጋት የተጀመረውን ውል-ተመስርቶ የሚሰራ የአቅርቦት ስርዓት አጠናክሮ መቀጠል እንደሚገባ ገልፀዋል።

በተጨማሪም የውጭ ምንዛሬን ለማዳንና ሀገራዊ አቅምን ለመጠቀም የሀገር ውስጥ መድኃኒት አቅራቢዎች እንዲጠናከሩ መደገፍ እንዳለባቸው ተጠቅሷል።

የስራ ከባቢን በቴክኖሎጂ በመደገፍ ምቹና የስራ ፍሰትን የሚያቀላጥፍ ሁኔታ ለመፍጠር የተጀመሩ ስራዎችን ማጠናቀቅ እንደሚያስፈልግም በግምገማው ተገልጿል።

በመጨረሻ፣ በግምገማው የተለዩ የአፈፃፀም እክሎችን በፍጥነት በማረም በቀሪ ወራት ተግባራዊ የድርጊት መርሃ ግብሮች እንዲተገበሩ ተስማምቶ ግምገማው ተጠናቋል።

አዲስ አበባ | ጥር 23፣ 2018 ዓ.ም
#ማገልገል ክብር ነው
በአማኑኤል ወርቃየሁ
Share this article:
🤖
EPSS Assistant Online · Ethiopian Pharmaceuticals Supply Service