260 ሺ ዶላር ዋጋ ያላቸው   የሕክምና መሣሪያዎች የጣሊያን መንግስት ለጤና ሚኒስቴር ድጋፍ አደረገ ፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨
News
February 04, 2026
127 views

260 ሺ ዶላር ዋጋ ያላቸው የሕክምና መሣሪያዎች የጣሊያን መንግስት ለጤና ሚኒስቴር ድጋፍ አደረገ ፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨

የህክምና መገልገያ ቁሳቁሶቹ በሆስፒታሎች የሚሰጠውን የድንገተኛ አደጋ ህክምና አገልግሎት፣ ምርመራ የማድረግና ሕይወት የማዳን ተግባር ይበልጥ በማጠናከር የጤና አገልግሎት ጥራቱን ከፍ ለማድረግ ትልቅ አቅም ይፈጥራሉ ብለዋል ዶ/ር መቅደስ።

የጣሊያን አምባሳደር በኢትዮጵያ ሴም ፋብሪ በበኩላቸው ኢትያጵያ በአጭር ጊዜ ውስጥ የማርበርግ ቫይረስን መቆጣጠር በመቻሏ የተሰማቸውን ደስታ ገልፀው፣ የዚህ የህክምና መሳሪያዎች እገዛ የሁለቱ ሃገራት ወዳጅነትና የሁለትዮሽ ትብብርን የበለጠ እንደሚያጠናክረው ገልጸዋል።

የሕክምና መሣሪያዎችና ቁሳቁሶች ልገሳ በኢትዮጵያ እና በጣሊያን መንግሥታት መካከል ያለውን የቆየና የጠነከረ የሁለትዮሽ ትብብር የሚያንጸባርቅ መሆኑን የኢትዮጵያ መድሃኒት አቅራቢ አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር አብዱቃድር ገልገሎ ገልፀዋል።
በፀሎት የማነ
#ማገልገል ክብር ነው!
Share this article:
🤖
EPSS Assistant Online · Ethiopian Pharmaceuticals Supply Service